Get Mystery Box with random crypto!

ይድረስ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት! * ሶርያውያን፣የመናውያን፣ደቡብ ሱዳናውያን፣ ኮንጓውያን እና ሌሎ | ETHIO ZENA (ኢትዮ ዜና)🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ይድረስ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት!
*
ሶርያውያን፣የመናውያን፣ደቡብ ሱዳናውያን፣ ኮንጓውያን እና ሌሎችም የሥራ ሁኔታ ተመቻችቶላቸው ጭምር በሰላም በሚኖሩባት ኢትዮጵያ፥ አማሮች በራሳቸው አገርና ምድር ዓይናችሁን ለአፈር እየተባሉ በጅምላ ይጨፈጨፋሉ። መነሻ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን፤ ይኼ ጉዳይ የአገር አንድነት እና ብሔራዊ ደኅንነት ስጋት ሆኖ በሁሉም ዘንድ እኩል ሊወገዝ ይገባው ነበር። በአገር ደረጃ ብሔራዊ የኃዘን ቀን እንዲታወጅ እና በወገኖቻችን ላይ የተፈፀመው ጭፍጨፋ የጋራችን ኃዘን እንዲሆን ደጋግመን ብንወተውትም ጉዳዩን ጉዳዬ ያለው አልተገኘም።

በዚህ ጉዳይ ዝም ብንል እንኳንስና ሰው፥ እግዚአብሔርም ይቅር አይለንም። ዝምታ ግፍና ግፈኞችን መተባበር ይሆናል። የሚመለከታችሁ አካላት ከመቅረት መርፈድ ይሻላልና ለራሳችሁ ስትሉ ኃዘናችንን በጋራ የምናደርግበትን ብሔራዊ ቀን አውጁልን። እንዴት የክብር ሞት እንነፈግ? እንዴት የክብር አፈር እንነፈግ?

(ለአገር አንድነት ስንል…ለመንግስታዊ ወግና ባሕሉም ስንል…ነው እንጂ ከልክ በላይ መታገሳችን፤ የወገኖቻችን ጅምላ ጭፍጨፋ ሳያሳዝነንና ሳይቆጨን ቀርቶ አይደለም! )