የሰርጥ አድራሻ:
ምድቦች:
ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች:
2.11K
የሰርጥ መግለጫ
🗣" በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 10:27)
🧑CREATER፦ Ⓓⓐⓝⓘⓔⓛ(@Bilxasor)
📩ለ አስተያየት📬፦ @Ethiowengelcomment_bot
🔎አድራሻ🔍፦ ወሊሶ...ብርሃን ለአለም ቤ/ክ (light for the world church)
Ratings & Reviews
Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.
5 stars
0
4 stars
1
3 stars
0
2 stars
1
1 stars
0
የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2
2022-02-20 17:46:26
818 voters849 views卂几丨乇ㄥ, 14:46
2022-02-20 17:46:26
916 voters812 views卂几丨乇ㄥ, 14:46
2022-02-20 17:46:26
855 voters790 views卂几丨乇ㄥ, 14:46
2022-02-20 17:46:26
863 voters774 views卂几丨乇ㄥ, 14:46
2022-02-20 17:46:26
860 voters759 views卂几丨乇ㄥ, 14:46
2022-02-20 17:46:26
806 voters754 views卂几丨乇ㄥ, 14:46
2022-02-20 17:46:26
870 voters747 views卂几丨乇ㄥ, 14:46
2022-02-20 17:46:26
817 voters764 views卂几丨乇ㄥ, 14:46
2022-02-20 17:46:26
806 voters781 views卂几丨乇ㄥ, 14:46
2022-02-14 22:40:20
"አንደበት እና ልብ"
ሞልቶ የፈሰሰ ከመስፈሪያው አልፎ፣
መለኪያ የሌለው እጅጉኑ ገዝፎ፣
መደምደሚያ አልባ አድማስ የሚሻገር፣
የሌለውን ነገር እንዳለ 'ሚፈጥር፣
ያንተ መኖር ለኔ የእኔ መኖር ነው፣
ይሄ ነው ትርጉሙ ሌላ ታሪክ የለው።
ህይወቴ በድሎት በጥጋብ ቢሞላ፣
ድህነት ቢያቆስለኝ
ከሰው መሀል ሆኜ ባጣ እንኳ ከለላ፣
ተስፋየን አጥቼ ወድቄ ብገኝ፣
እንደሰው 'ሚያስቆጥር ምንም ባይኖረኝ፣
በባዶው አለሜ አንተው ትበቃለህ፣
በድቅድቁ ሌሊት ቀንን ታወጣለህ፣
አንተ እኮ ጌታ ሆይ
አንድ ሆነህ እልፍ ነህ!
እያልኩ እቆይና
ድንገት ብርሀኔ ጭልምልም ሲልብኝ፣
አንድ ራሴን ሆኜ ሰው ሲናፍቀኝ፣
ያለኝንም ሁሉ ነፋስ ሲበትነው፣
አንተን ማየት ትቼ
ወዲያና ወዲህ ስዞር እገኛለሁ።
*
ፍቅርህ በርትቶብኝ አቅም አጥቻለሁ፣
የኔ አለም ጠቦኝ ባንተ ገብቻለሁ፣
ሀዘኔን አራግፈህ ደስታን ሰጥተኸኛል፣
ካንተ ውጭ ለኔ እንዴት ይታየኛል?!
አንተ ማለት ለኔ
የማያልቅ ደስታየ ሀዘን የሌለበት፣
ሁኔታን የማያይ የአለምን ድሎት፣
እርከን የሌለው ነው ጌታ ያንተ ደስታ፣
እልፍ ያለ ነገር ከአለም እርካታ።
በእርሻዎች መሀልም መብል ባይኖረ፣
በለስ ባታፈራ ወይንም ባይገኝ፣
በነገሮች ስኬት መች ሆነ ደስታየ፣
ከውስጤ የሚፈልቅ ምልክት ያላየ፣
ችግር የሚገፋ
የአ'ምሮ ረፍት ሳቄ ነህ ጌታየ።
እል እልና
መደሰቻ ምክንያት መስሎኝ ሁኔታየ፣
እድልን ሰጠሁት ለምኞት ስጋየ።
በፀሎት በቃልህ 'ማገኘውን ሀሴት፣
በማይጠቅመኝ ነገር በዲናር ለወጥኩት።
ባለሁበት ቤት ውስጥ የጎደለኝ መስሎኝ፣
እጆቼን ሰድጄ እርካሽ ቃረምኩኝ፣
ያንተን ክብር ትቼ የኔን አሳደድኩኝ።
**
ዘመኑ አርጅቷል 'ያለም ኑሮ ይብቃኝ፣
ቶሎ ናልኝና
ለሰማዩ መንግስት ለፂዮኔ አብቃኝ፣
የዚች ምድር ነገር ምኞቷ ከንቱ ነው፣
'ካንተ ጋር ይሻላል መሞትም ጥቅሜ ነው።
አሜን ማራናታ ጌታ ሆይ ቶሎ ና፣
ናፍቄአለሁና
ከመላእክቱ ጋራ አንተን ላመሰግን ልሰዋ ምስጋና።
ይልና አንደበቴ፣
የተጀመረውን የምድር ህይወቴ፣
ያልጨረስኩት ትምህርት ያልጀመርኩት ፍቅር፣
ትውስ ይለኝና
ገና ያልተነካ ብዙ እንዳለኝ በር፣
'አይይ አምላኬ ሆይ ብትቆይ ይሻላል፣
ትንሽ ብትጠብቅ ለአንተም ይበጃል፣
አሁን በዚህ ሰዐት ብዙ ሰው አልዳነም፣
ኧረ እንደውም ስልህ አንተን አያውቁህም፣
አሁን እንኳ አትምጣ ትንሽ ጊዜ ስጠን፣
እንድንቀበልህ በሙሉ ልባችን'፣
ብሎ ይፈርጃል እንደገና ልቤ፣
መስነፊያየ ምክንያት በዝቶብኝ ሰበቤ።
እኔ ማለት እንዲህ እንዲህም እኔ ነኝ፣
ልቤና አንደበቴ 'ማይገናኙልኝ፣
ልቤ ቀኙን ሲመርጥ ምላሴ የግራ፣
ግራውም ይሁን ስል ቀኙን የማወራ፣
ከመሀከል የቆምኩ ምስኪን ፍጥረት ነኝ፣
መንትያ መንገዱን መነጠል ያቃተኝ።
አንድየ ተለመነኝ፣
ፀሎቴን ስማ ባክህ አድምጠኝ፣
እንደልቤ ሳይሆን ምላሴን አኑረኝ
By. Eliyas
༶•┈┈⛧┈♛ ♛┈⛧┈┈•༶
@christ_is_life
@christ_is_life
@christ_is_life
•┈┈⛧┈♛ ♛┈⛧┈┈•
∆∆∆∆share∆∆∆∆
1.5K views卂几丨乇ㄥ, 19:40