Get Mystery Box with random crypto!

ዮሴፍ ወደ ግብጽ የወረደው፣የሄደው ወንድሞቹ ስለሸጡት፣ስለገፍቱ፣ስለላኩት ሳይሆን፤እግዚአብሔር ስለ | ኢትዮ_ወንጌል || Ethio_Wengel

ዮሴፍ ወደ ግብጽ የወረደው፣የሄደው ወንድሞቹ ስለሸጡት፣ስለገፍቱ፣ስለላኩት ሳይሆን፤እግዚአብሔር ስለ ሰደደው እና ስለላከው ነው።"አሁንም እናንተ ወደዚህ የላካችሁኝ አይደላችሁም እግዚአብሔር ላከኝ እንጂ.."ዘፍጥረት 45: 8
እግዚአብሔር ዮሴፍን ወደ ግብጽ የሰደደው ዮሴፍ ከመወለድ ከረጅም አመታት በፊት ለአብርሀም የነገረውን #የትንቢት ቃል ፍጻሜ በዮሴፍ ሊጀምር ሰለወደደ ነው።"ዘርህ ለእርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንዲሆኑ በእርግጥ እወቅ ባሪያዎች አድርገውም አራት መቶ ዓመት ያስጨንቋቸዋል።"ዘፍ15:13 ይህንን የትንቢት ቃል ሊፈጽምበት ዘንድ እግዚአብሔር የዚህ የትንቢት ቃል መነሻ፣ማስጀመርያ፣መንገድ ጠራጊ ይሆን ዘንድ ነበር የላከው።ይህ ወደ ግብጽ መግባት፣ባርነት ደሞ ወደ ከነዓንን መውጫ መንገድ ነበር።

ዮሴፍ ግብጽ ከገባ ከረጅም ጊዜዬ በሀሏ የእስራኤል12ቱም ነገዶች ወደ ግብጽ ገቡ።ዘፍ 46:1-26፤ዮሴፍ እንደሚነግስ አየ እንጂ መች ግብጽ እንደሚወርድ፣እንደሚሄድ አየ፤ዮሴፍ ያላሰበበት፣ያልመረጠበት ሀገር የመሄድ፣የመውረድ ምስጥር የሚያውቀው ሰማይ ብቻ ነበር።ምስጥሩም ለአብርሀም የነገረውን ትንቢታዊ ቃል ፍጻሜ በዮሴፍ ሊጀምረው ነው።
"ሳትመርጡ በእግዚአብሔር ከተመረጠላችሁ፤ሳትወድ በእርሱ ከተወደደላችሁ ሳታስብ እርሱ ካሰበላችው የገባችሁበት ቦታ የመለኮት አላማ አለበት።

by. DANIEL (@Bilxasor)
╔════ஜ۩۞۩ஜ════╗
@ethiowengel @word_of_god1
@ethiowengel @word_of_god1
@ethiowengel @word_of_god1
╚════ஜ۩۞۩ஜ════╝
⇘⇘⇘⇘⇘SHARE⇘⇘⇘⇘⇘