Get Mystery Box with random crypto!

#ስለ_ቀናተኞች_ትምህርት ቀናተኞች ሮማውያንን ይጠሉ ነበር። በሃይማኖት በኩል የፈሪሳውያን እምነ | ኢትዮ_ወንጌል || Ethio_Wengel

#ስለ_ቀናተኞች_ትምህርት

ቀናተኞች ሮማውያንን ይጠሉ ነበር። በሃይማኖት በኩል የፈሪሳውያን እምነት ይቀበሉ ነበር ፤ ፈሪሳውያን የመጀመሪያው ፖለቲካ ስለማይፈልጉ ይንቋቸው ነበር ። ቀናተኞች ሮማውያንን
በዓመፅ፤ በተንኮልና በማሸበር ሊጥሏቸው ሞከሩ። የመጀመርያው ዓመጽ 6 ዓ.ም በይሁዳ ገማላ መሪነት የተከናወነውና የከሸፈው ነበር።

ቲቶ ኢየሩሳሌምን ሲወርር ጸብ ለመመሥረት ተፈጥረው ከነበሩት ቡድኖች አንዱን የመሠረቱት እነርሱው ነበሩ። ለኢየሩሳሌም ውድቀት ከፍተኛ ምክንያት የሆነው እነርሱ የፈጠሩት ጸብ ነው፤

ከኢየሱስ ደቀ መዛሙርት አንዱ የነበረው ስምኦን ከቀናተኞች ወገን ነበር፤ ሉቃ. 6፡ 15፤ ሐዋ. 11፡13። ቀናተኞች በሐዋ.21፡38 ከተገለጸው ነፍስ ግድያ ጋር ተባባሪነት ሳይኖራቸው አይቀርም። የእሥራኤል እውነተኛ አምላክ በሆነው በእግዚአብሔር ላይ ማመጽ ነው እያሉ ጣኦት ከሚያመልኩ ወገን ለሆነ ንጉሥ እሥራኤላውያን ግብር መክፈላቸውን ይቃወሙ ነበር። በ6ዓ.ም ያነሡት ዓመጽ ከከሸፈ
በኃላ እንኳ ለ60 ዓመታት ያህል ጽብ ላማንሣት አድብተው ይጠብቁ ነበር።

በማሳዳ የነበራቸው የመጨረሻው ብርቱ ምሽግ በ73 ዓ.ም ተመታ።

by. DANIEL (@Bilxasor)
╔════ஜ۩۞۩ஜ════╗
@ethiowengel @word_of_god1
@ethiowengel @word_of_god1
@ethiowengel @word_of_god1
╚════ஜ۩۞۩ஜ════╝
⇘⇘⇘⇘⇘SHARE⇘⇘⇘⇘⇘