Get Mystery Box with random crypto!

Wollo University መገኛ፡ደሴ( አማራ) የግቢ ብዛትና የአየር ሁኔታ፡ ዩንቨርሲቲው ሁለት | 🇪🇹ኢትዮ University

Wollo University

መገኛ፡ደሴ( አማራ)
የግቢ ብዛትና የአየር ሁኔታ፡ ዩንቨርሲቲው ሁለት ግቢዎች ያሉት ሲሆን እነሱም ደሴ ከተማ እና ኮምበልቻ ከተማ ላይ ይገኛሉ፤ ሁለቱ ከተሞች በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙ ከተሞች ቢሆኑም የአየራቸው ፀባይ ግን ለየቅል ነው።
ደሴ ከተማውም በመጠኑ ብርዳማ ሲሆን ግቢው ደግሞ ትንሽ ከከተማው ወጣ ብሎ ስለሚገኝና ሰፈሩም ዛፍ ነገር ስላካበበው የብርዱ መጠን ጠንከር ይላል በተለይ ምሽት ላይ ወዝወዝ ያስደርጋል ።
ኮምበልቻ ከተማ ደግሞ የኢንዱስትሪ ከተማ ስለሆነች መሰለኝ ሞቅ ትላለች ምናልባት የፋብሪካው ጢስ ይሆን?
ለማንኛውም ኮምቦልቻ ግቢ ለምትመደቡ ተማሪዎች ቀን ቀን ሞቃታማ ማታ ማታ ደግሞ ከዶርም ወጣ ሲሉ ብርዳማ ግቢ ነው ።
ኮቻ ግቢ ልክክ በልክ ነገር ናት ማለት ግቢው በጣም ሰፊ ሚባል ነገር አይደለም geographical አቀማመጡ ለተማሪዎች ሳይሆን ለወታደሮች ተብሎ design የተደረገ ሊመስላቹህ ይችላል ቢሆንም ግን ፍቅር ፍቅር ከሚሸቱት የግቢው ማህበረሰብ (ተማሪዎች) ተመጣጣኝ ካሳ ይጠብቃቹሃል።
፩ ደሴ campus (main campus)
ሁሉም የማህበራዊ ሳይንስ ትምህርቶች የሚገኙበት ሲሆን በተጨማሪም ከተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ውስጥ የጤናውን(medicine, nursing,HO..) እና የቲቺንግን(biology, physics, chemistry..) እና የቋንቋ ትምህርት (አረብኛ፣አማርኛ..)ክፍሎች የያዘ ግቢ ነው።
፪ kombolcha institute of technology
ከስሙ መረዳት እንደሚቻለው ግቢው የቴክኖሎጂ ግቢ ነው
በውስጡም
Engineering, computer science, fashion design and architecture የመሳሰሉትን መስኮች አቅፎ የያዘ ግቢ ነው
Engineering
- Electrical and computer engineering
- Mechatronics Engineering (robotics)
- Software engineering
- Mechanical Engineering
- Civil engineering
- Textile engineering
- water resources and irrigation Engineering
- Hydrolics Engineering
- Industrial Engineering
- Cotem
- Garment Engineering
- Leather Engineering
- Chemical engineering...
በቀጣይ ምናልባትም Biomedical engineering ሊጀምር ይችላል።
Computer science
#CS
#IS
#IT
Fashion design and architecture
የትምህርት ሂደቱ አሪፍ የሚባል ነገር ነው ቢሆንም ግን ትንሽ ያጨናንቃል ።
በግ ተራ፣ኦቨር፣ጨብሲ ምናምን ለሚያበዛ ተማሪ የግቢው የክብር መሸኛ ደብዳቤ ይበረከትለታል ( ትምሮ ፊት ይነሳዋል)
በተረፈ ግቢያችን ከዘረኝነት የፀዳ ነው እንዳልል ከኢትዮ ውጭ ያለ ዩንቨርሲቲ ስለሚያስመስልብኝ በአንፃራዊነት ከሌሎች ግቢዎች በተሻለ መልኩ ሰላማዊ ግቢ ነው ለማለት ይቻላል።(ኮሽ ብሎ አያቅም )

ኮምቦልቻ ግቢ ለምትመደቡ ተማሪዎች ግቢው የሚገኘው አስፓልት ዳር በመሆኑ ግቢ በር ላይ በመውረድ ከመናሀሪያ ትርምስ ትድናላቹህ

ደሴ ግቢ ለምትመደቡም ሰርቪሶች ስለሚመደቡ ብዙ አታስቡ ፤ለማንኛውም ግን ንብረታችሁን ጠንቀቅ በሉ ምክንያቱም መናሀሪያ መግባታቹህ ስለማይቀር ብዬ ነው።
ወሎ ዩኒቨርሲቲ ስትደርሱ የተማሪዎች ህብረት ፣ የተማሪ ፖሊስ፣ቻሪቲ ክበብ፣ የሰላም ክበብ .. ወዘተ አባላት በር ላይ ባጅ አጥልቀው ስለሚቀበሏቹህ ምንም ዓይነት ሀሳብ አይግባቹህ ።

በተረፈ ወደ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ተመድባቹህ ለምትመጡ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ወደ ፍቅር ካምፓስ መጡ ብለን በወሎኛ እቅፍ አርገን ስመን እንቀበላቹሃለን

ወሎ ገራገሩ
ሸጋ ነው ሀገሩ


ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  @ethiouniversity1bot

            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝