Get Mystery Box with random crypto!

Debrebirhan University መገኛ፡ደብረ ብርሃን ርቀት ከአ.አ ፡ 130km የጉዞ ሰአ | 🇪🇹ኢትዮ University

Debrebirhan University

መገኛ፡ደብረ ብርሃን
ርቀት ከአ.አ ፡ 130km
የጉዞ ሰአት : 1:30-2:30(mostly)
የአየር ሁኔታ ፡ በጣም ቀዝቃዛ ነገር ግን ግንቦት አካባቢ ለቲሸርት አመቺ ነው ጠዋት እና ማታ ግን በየቀኑ ብርድ አይቀሬ ነው፡፤ ደብዬ ውስጥ በተለይ ጥቅምት አብዝቶ ደሞ ሕዳር ላይ ያለው ብርድ እንኳን ለሰው ልጅ ለእቃም አይመከርም በጣም ከፍተኛ ብርድ አለ ስለዚህ ተማሪዎች እዚህ ከመጡ በጣም ወፍራም ብርድልብስ ወፍራም ልብሶች ግድ እና ግድ ነው፡፡

ግቢ ብዛት :- 1 ከከተማም የ 3ብር ታክሲ ነው ለከተማው ቅርብ ሲሆን ነገር ግን ጤናዎች መማሪያ ከግቢ ውጪ ነው ማደሪያቸው ግን ከሁሉም ጋር ተመሳሳይ ነው፥ ለት/ት ጊዜ ግን ወደ class መግቢያና መውጫ ሰአቶች ላይ የግቢ Bus የሰርቪስ አገልግሎት ይሰጣቸዋል

የEnginering ሳይንስ department ብዛት: 7
Electrical and computer
engineering
Mechanical engineering
Civil engineering
COTM (construction
technology management)
Industrial engineering
Chemical engineering
food engineering


የምግብ ነገር ብዙም አያሳስብም
ግቢ ውስጥ ሁለት አዳራሽ ያለው የጊቢ ካፌ እና ሶስት ላውንቾች ይገኛሉ

የዋጋ ሁኔታ፡- ምግብ በላውንች ከ10.00-22.00 ብር ነው
ሽሮ ,ተጋቢኖ,ፓስታ ስልስ በአትክልት,ፍርፍር,በየአይነት, ....., ቀይወጥ, ቅቅል,ስጋፍርፍር በላውንች (optional) ነው የሚኖርበት ግዜ አለ የማይኖርበት ግዜ አለ

ምግብ ከግቢ ውጪ:-
ከ20-40 እንደምግቡ አይነት ግን ውጪ የሌለ የለም በፆም አንዳንድ ቤቶች ሽምብራ አሳ እራሱ ይገኛል በር ላይ ብዙ ቤቶች አሉ ::
ነገር ግን ከዳቦና ቦንቦሊኖ ውጪ እንደ ኬክ ፣በርገር ምናምን ከተማ ያገኛሉ

ሻይ 1.00
ዳቦ 2.00
ቦንቦሊኖ 2.00

ግቢው ውስጥ የሚገኙ ሌሎች አገልግሎቶች
1. ላውደሪ
2. ፀጉር ቤት
3. አነስተኛ ሱቆች (not mini market, not super market) ነገር ግን ብዛት ነገር አላቸው መገኛቸው ለወንዶች ቅርብ Block 34 ለሴቶች ቅርብ ዶርሚተራቸው መውጫ ላይ


ማስጠንቀቂያ፡
በጣም አስፈሪ የሚባሉ ሰፈሮችን ሳልጠቀስላቹህ ባላልፍ ደስ ይለኛል
የ04 ሰፈር ልጅ ከተባለ በሩቁ መሸሽ ነው ጨዋታቸው ከስለት ጋር ስለሆነ በተጨማሪ የጠባሴም ልጆች ፀብ ከተነሳ አይቻሉም ይህን ያልኳቹህ እንድትረበሹ ምናምን ሳይሆን አብዛኛውን ግዜ fresh ቀልቃላ ስለሆነና መግቢያ መውጫውን በማያውቀው ሰፈር በመሄድ ችግር ስለሚደርስበት ነው። እንዲሁም አንዳንዶቹ ደግሞ club ለመውጣት ይቋምጣሉ ከላይ የተጠቀሱት ሰፈር ልጆች ደግሞ መዋያቸው እዛ ነው ባይገርማቹህ 2011 (fresh) ላይ
ክለብ ለክለብ የሚዞሩ ልጆች ስልክ እና ብር ተወስዶባቸዋል በተጨማሪም ብርዱ እንዳይሰማቸው አንድ ሁለት ጥፊ....
ያስተውሉ የዚህ ገፈት ቀማሾች 95%ቱ ኦቨር የሚወጡት ናቸው። (መጠጥ ጠጥቶ ቦክስ ከመጠጣት F መጠጣት ይሻላል)

ሌላው ደግሞ ግቢው እንደ አምናው ከሆነ ትራንስፖርት ላምበረት መናኀሪያ( አዲስ አበባ) ያዘጋጃል ማለትም ከአ.አ እስከ ግቢ ድረስ በ ግቢ Bus በነፃ
ሲገቡ ተማሪ ሕብረቶች እና ክበባት አቀባበል ያደርጉላቸዋል ብሎካቸውንም ያሳዩአቸዋል የሚያጡት ከሆነ ግን
ወደ Dorm መታጠፊያዎች ዋና ዋና መስመሮች ላይ ይለጠፋል፡፡
ማለፍ የማልፈልገው አሳሳቢ ጉዳይ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ማለትም የትኛውም ግቢ ለምትገቡ ተማሪዎች በሙሉ አደራ ብዬ የምላቹህ ነገር የዘረኝነትን ነገር ነው፤ ባሁኑ ወቅት ዩንቨርሲቲዎቻችንን ብሎም ሀገራችንን እየተፈታተናት ያለው ነገር ጠባብነት ነው ፡ ከዘረኝነት በላይ ደግሞ ጠባብነት የለም ።
በፈጠራቹህ Rational ለመሆን ሞክሩ።

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  @ethiouniversity1bot

            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝