Get Mystery Box with random crypto!

Mekelle University መገኛ፡ መቀሌ የአየር ሁኔታ፡ እስከ የካቲት መካከለኛ ብርድ በጥዋ | 🇪🇹ኢትዮ University

Mekelle University

መገኛ፡ መቀሌ
የአየር ሁኔታ፡ እስከ የካቲት መካከለኛ ብርድ በጥዋቱ ክፍል ያለ ሲሆን አመሻሽ ላይ ትንሽ ነፋስ ነገር አለው ይበርዳልም ያው ሙቀት ሚባል ነገር አያስቸግርም ቢባል ይሻላል።ግንቦት አካባቢ ግን ሙቀት ይኖራል።በተለይ engineering,comptional&agri ሚደርሳችሁ ተማሪዎች ግቢያቹ ነፋሻማ ና ብርድም ጭምር ስላለው ሹራብ ነገር ያስፈልጋቹሃል።

በውስጡ ያሉት ግቢዎች፡ አምስት ሲሆኑ እነሱም

እንዳየሱስ(ኣሪድ) ዋናው ግቢ ሲሆን በውስጡም የተለያዩ የትምህርት መስኮች ይሰጣሉ
Engineering science
Comptional science
Agricultural science
Some social dep'ts(like hotel and managment)

Software engineering መማር ለምትፈልጉ pre engineering ሳትማሩ entrance resulታቹህ ከ450 በላይ ከሆነ join ማድረግ ትችላላቹ።(450 ያለፉት አመታት ነው ዘንድሮ ምናልባት ሊቀንስ or or)

የ ARCHITECT AND URBAN PLANNING ትምርቶችም pre engineering ሳትማሩ በቅድመ ፈተና መቀላቀል ትችላላችሁ።
በነገራቹህ ላይ ግቢው የሚገኘው ከተማው መግቢያ አከባቢ በመሆኑ መናሀሪያ ድረስ መሄድ አይጠበቅባችሁም ግቢ በር ላይ መውረድ ይቻላል።
ዓይደር ግቢ የhuman health ነክ
Like
medicine
Health oficcer
Dental medicine
Anstesia etc...ይሰጣሉ።

ዓዲ ሓቂ ግቢ-የsocial science ግቢ ነው። በውስጥ ያሉ የትምህርት መስኮች
law
Economics
Management
Accounting etc... ናቸው

ዓዲ ሓውሲ ግቢ-የእንስሳት ህክምና ክፍል ትምርት ሚሰጥበት ግቢ ነው።
Like
veternary medicine
Veternary science etc...

ኣይናለም ግቢ
ይሀኛው ግቢ like ASTU & AASTU መግቢያ ፈተና ያለው ሲሆን በውስጡም computer , IT, electrucal & chemical
ያሉትን ያቀፈ ሲሆን የፈተናው ምዝገባ በቲቪ ማስታወቂያ ይነገራል እናም በደምብ ተከታተሉ በተለይ በcomputer ዙሪያ ትምርት ለምትፈልጉ ተማሪዎች አሪፍ ግቢ ነው መግቢያ ፈተናውም ቀለል ነው።
How was price of food

የምግቧን ነገር አጠይቁኝ ዋው ነው ፤ ግቢ ዉስጥ የሚፈልጉትን ኣይነት ምግብ በተመጣጣኝ ዋጋ በሚገራርሙ restaurantኦች ያገኛሉ።
ሽሮ ፣በየኣይነት ፣ፓስታ በስጎ ወይም በአትክልት፣ በአንቁላል፣ ፍርፍር/ስልስ ምናምን ከ12-25ብር ብቻ ፨

ሳንድዊች ፡ በርገር ፡ቺፕስ፡ ዶናት፡ቦንቦሊኖ፡ኬክ ምናምንም እንደዚሁ በማይታመን ዋጋ ይገኛሉ

ምንችት፡ጥብስ፡ጥብስ ፍርፍር ቀይወጥ ምናምን ደግሞ ከ25-30ብር

ሻይ-2ብር
ቡና-5ብር
ለስላሳ-10ብር

አንዳንድ ሸቀጦች ካስፈለጓቹህም ፀዳ ያሉ supermarketኦች አሉ።

ከተማም ቢሆን ምርጥ ምርጥ ምግብ ቤቶች አሉ የግቢ ተማሪዎች ብቻ ሚጠቀሙባቸው ያው ከሌሎቹ በጣም ቅናሽ ናቸው በደምብ ፈታ ትላላቹ።
የግቢው ካፌ ዝርዝር ምግብ ከፈለጋቹ ካፌ ምንሼ ሚል app Download ኣርጋቹ ማየት ትችላላቹ።
ትንሽ ለአዲስ ተማሪዎች አስቸጋሪ የሚሆነው የውሃው ነገር ነው፤ ውሃውን እስከምትለምዱት ድረስ 20L packed water በ75 ብር ገዝታቹህ ተጠቀሙ ።
ፀጉራችሁንም ስትታጠቡ ሻምፖ ነገር ብትጠቀሙ አሪፍ ነው ፀጉራቹህ እንዳይሰባበርና እንዳይነቃቀል፥ በተለይ ለሴቶች ፀጉራችሁን ስለምትሳሱለት


መቐለ መነሃሪያ እንደገባቹህ service ተዘጋጅቶ ይጠብቃቹሃል የትምህርት ክፍላችሁን( department) አየተናገራቹ ወደየግቢያቹህ ይወስዷቿሃል ግቢ ስትደርሱም ሚገርም አቀባበል ይጠብቃቹሃል። በተጨማሪም ከተለያዩ ክበባት የተውጣጡ ተማሪዎች ዶርም ይወስዷቿል።እናም ብዙ አትቸገሩም፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
Welcom fresh sts. ....
For more info. Just visit The website
www.MU.edu.et

በመጨረሻም ለአዲስ ተማሪዎች ስለ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ማንኛውም አይነት ጥያቄ ካላቹህ እናንተን ለመተባበር ፍቃደኛ የሆኑ ምርጥ ምርጥ ነባር ተማሪዎች ስላሉ ሃሳብ አይግባቹህ

ምደባ ከወጣ በኋላ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ለሚደርሳቹህ ተማሪዎች የተለየ ድጋፍ ከነባር ተማሪዎች ተሰናድቶላቹሃል ።

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  @ethiouniversity1bot

            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝