Get Mystery Box with random crypto!

ጅማ ዩኒቨርስቲ ጅማ ዩኒቨርሲቲን ለሚሞሉ #የ12ኛ_ክፍል ተማሪዎች መረጃ ጅማ ከ አ.አ | 🇪🇹ኢትዮ University

ጅማ ዩኒቨርስቲ

ጅማ ዩኒቨርሲቲን ለሚሞሉ #የ12ኛ_ክፍል ተማሪዎች መረጃ
ጅማ ከ አ.አ 346km እርቀት ላይ ይገኛል።

የአየር ንብረት ምቹ የሆነ አካባቢዉ በአረንጒዴ የተሸፈነ

አራት ካምፓሶች አሉት አራቱም ከተማ ዉስጥ ናቸዉ በአጋሮ ከተማ አምስተኛ ካምፓስ ተገንብቱዋል ተማሪ አልገባበትም
ግቢ ዉስጥ ሁሉም የተሙዋላ ነዉ ዉሀ 100% በሚባል ደረጃ አይቸግርም
ዋይፋይ በሔድንበት ቦታ ሁሉ አለ
መብራት አይሔድም ቢሔድም ወዲያዉኑ ጀኔሬተር ይበራል አያሳስብም።

የማይሰጠዉ ፊልድ የለም በተለይ #ጤና ለሚመርጡ ሁሉም የተሙዋላ ነዉ እራሱን የቻለ የቴክኖሎጂ ካምፓስም ስላለዉ በፊልድ ጉዳይ አታስቡም።

በግቢ ጥራት ታላቅነቱን ያስመሰከረ ግቢ ነዉ
የመጀመሪያዉ ትዉልድ ዩኒቨርሲቲ ነዉ
የፀጥታ ጉዳይ 2012 ላይ ሁከት ነበር ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃትም ነበር
እኔም የዚሁ ሰለባ ነበርኩ ትምህርቴን እምቀጥልም ከእናንተ ከአዲስ ገቢዎች ጋር ነዉ የ2012ቱ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የፀጥታ መደፍረስ ግን በጅማ ብቻ ሳይሆን እንደ ሀገር በአብዛኛዎቹ ዩኒቨርሲቲዎች ነዉ ብዙ ተማሪም እኔን ጨምሮ ከትምህርት ገበታዉ ተፈናቅሉዋል ከአዲስ ገቢዎች ጋር ጥሪ እንደሚደረግልን ተነግሮናል ወደፊት ግን የፀጥታ ችግር እንደማይኖር ተስፋ አለኝ የጅማ ከተማ ማህበረሰብ ግን በጣም የዋህ እና እሩህሩህ ሰላምን የሚወድ ነዉ ከየትም ና ከየት ከተማ ዉስጥ እንደፈለክ መንቀሳቀስ ትችላለህ የግቢ ተማሪ ከሆንክ ሊረዱህ ይሞክራሉ እንጅ አያዋክቡህም ባይኔ ያየዉት ነገር ሥለሆነ ነዉ።

የሌሎች ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዚሁ መልኩ ፃፉልን

መረጃውን ያደረሰንን ከልብ እናመሰግናለን።

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  @ethiouniversity1bot

            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝