Get Mystery Box with random crypto!

በፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ዳሞት መሰናዶ ቁጥር 1 ት/ቤት ላይ በተፈፀመ የቦምብ ጥቃት በ | 🇪🇹ኢትዮ University

በፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ዳሞት መሰናዶ ቁጥር 1 ት/ቤት ላይ በተፈፀመ የቦምብ ጥቃት በ31 ተማሪዎች ላይ ጉዳት ደርሷል የፍኖተ ሰላም ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ገልጿል

በቦምብ ጥቃቱ 6 ተማሪዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ሙሉዓም ገሰሰ ገልፀዋል።

የቦምብ ጥቃቱ ትላንት ማለትም መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 2፡30 ሰዓት መፈፀሙን የተናገሩት ምክትል ኮማንደሩ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው 6 ተማሪዎች ለከፍተኛ ህክምና ሪፈር ተፅፎላቸው የህክምና ክትትል እያገኙ ሲሆን 15 ተማሪዎች ደግሞ በፍኖተ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል ህክምና እያገኙ ናቸው ብለዋል።10 ተማሪዎች ላይ ደግም ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል ነው የተባለው።

አደጋውን ተከትሎ አንድ ተጠርጣሪ ተማሪ መያዙን የገለፁት ምክትል ኮማንደሩ በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጽ/ቤቱ እየሰራ መሆኑን ምክትል ኮማንደር ሙሉዓለም ተናግረዋል ሲል የዘገበው የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ነው።

(መናኸሪያ ሬዲዮ)
ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝