በትግራይ ክልል በትምህርት ገበታ ላይ ያለው የተማሪ መጠን
41 በመቶ ብቻ መሆኑ ተገለፀ፡፡
በክልሉ በትምህርት ገበታ ላይ መሆን ከሚገባቸው
2.4 ሚሊዮን ተማሪዎች
994,369 ተማሪዎች (
41.1 በመቶ) ብቻ በትምህርት ላይ እንደሚገኙ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የመቐለ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገልጿል፡፡
ተማሪዎቹ በትምህርት ገበታቸው ላይ ያልተገኙት በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት እንደሆነ ጽ/ቤቱ አስረድቷል፡፡
ጽ/ቤቱ በ
22 ወረዳዎች በሚገኙ
794 ትምህርት ቤቶች ላይ በተደረገ ክትትል
112 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ፥
595 በከፊል እንደተጎዱ ጠቁሟል፡፡
ከ
794 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ምንም ዓይነት ጉዳት ያልደረሰባቸው
47 ትምህርት ቤቶች ብቻ እንደሆኑ የጽ/ቤቱ ኃላፊ ፀሀዬ አንባዬ ለሸገር ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በክልሉ መዲና መቐለ ባደረገው ክትትልም በ
24 ትምህርት ቤቶች ተፈናቃዮች መኖራቸውን አረጋግጫለው ብሏል፡፡ #SheferFM
ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1
@ethiouniversity1
@ethiouniversity1
╚═══════════╝