Get Mystery Box with random crypto!

በኦሮሚያ ክልል መሬት ያልወሰዱ መምህራን የመኖሪያ ቤት የሚሰሩበት መሬት እንዲሰጣቸው ታዘዘ በኦሮ | 🇪🇹ኢትዮ University

በኦሮሚያ ክልል መሬት ያልወሰዱ መምህራን የመኖሪያ ቤት የሚሰሩበት መሬት እንዲሰጣቸው ታዘዘ

በኦሮሚያ ክትል የመኖሪያ ቤት የሚሰሩበት መሬት ላልወሰዱ የክልሉ መምህራን ቦታ እንዲሰጣቸው የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ትእዛዝ መስጠታቸውን የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

የክልሉ የትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በአዳማ ከተማ ውይይት አድርጎ 8 የውሳኔ ሀሳቦችን ያስተላለፈ ሲሆን ከ8ቱ ነጥቦች አንዱ በከተማ ቤት መስሪያ ቦታ ላልወሰዱ መምህራን በአስቸኳይ ሊሰጣቸው ይገባል የሚል እንደሆነ ተጠቅሷል።

ከዚህ ቀደም መምህራኑ የቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው መመሪያ ወጥቶ እንደነበር የተጠቀሰ ሲሆን ከቆይታ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች እገዳ ተጥሎ እንደነበርና በክልሉ ት/ት ቢሮ ጥያቄ መሰረት ዳግም የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ለመምህራኑ እንዲሰጣቸው ትእዛዝ መሰጠቱ ተጠቁሟል። ጉዳዩም ተፈፃሚ እንዲሆን የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ለተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ትዕዛዝ መስጠቱም ተገልጿል።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝