Get Mystery Box with random crypto!

ንግድ ባንክ የማስጠንቀቂያ ቀነ ገደብ ሰጠ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወ | 🇪🇹ኢትዮ University

ንግድ ባንክ የማስጠንቀቂያ ቀነ ገደብ ሰጠ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ወይም ወደተለያየ ሂሳቦች ያስተላለፉ ግለሰቦች እስከ መጪው ቅዳሜ (መጋቢት 14/2016) ድረስ በፈቃዳቸው እንዲመልሱ ቀነ ገደብ አስቀመጠ።

ይሁን እንጂ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ተጠቅመው አላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ተመላሽ የማያደርጉ ግለሰቦች ላይ ደረጃ በደረጃና በተከታታይ የተለያዪ ጠንከር ያሉ እርምጃዎች ለመውሰድ እንደሚገደድ ገልጿል።

ባንኩ አያይዞም ከታቀዱት ዋና ዋና እርምጃዎች መካከል የሚከተሉት እንዳሉ እንዲታወቁ ይፈለጋልብሏል:-

1. ከሕግ አካላት ጋር በመተባበር የግለሰቦችን ሥም ዝርዝር በየቅርንጫፎች እና እንደሁኔታው ግለሰቦቹ ሊታወቁ በሚችሉበት ኣካባቢ ይፋ በማድረግ ቀጣይ ሕጋዊ እርምጃዎችን እንዲቀጥሉ እንደሚደረግ እንገልጻለን፡፡

2. ⁠ከዚህ በላይ በተጠቀሰው እርምጃ መሰረት አሁንም ቀርበው የማይመልሱ ከሆነ በሕጋዊ ሂደቱ ተገቢው ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በድርጊቱ የተጠረጠሩትን ግለሰቦች ፎቶግራፋቸውን እና ዝርዝር ማንነታቸውን የሚገልፁ መረጃዎች ባንኩ በመረጠው የብዙሀን መገናኛ መንገድ ለሕዝብ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን ያሳስባል፡፡

3. ⁠ከእርምጃዎቹ ጎን ለጎንም ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ የወሰዱትን ገንዘብ እስከ ቅዳሜ ተመላሽ የማያደርጉ ግለሰቦችን ከፍትህ አካላትና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር ተገቢውን የወንጀል፣የፍትሐ ብሔርና አስተዳደራዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ እንደሚያደርግ አስጠንቅቋል።
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝