Get Mystery Box with random crypto!

በፍቅር ጦር ሞትን ስትገድል የነበረች ደግማ ደግማ እንከፍ ክንፉን የሰበረች የደግነት መልክ አም | ጠይም | Teyim 🌹

በፍቅር ጦር ሞትን ስትገድል የነበረች
ደግማ ደግማ እንከፍ ክንፉን የሰበረች
የደግነት መልክ አምሳሉ
የቸርነት ወዝ ጸዳሉ
ክንፋም እናት ብትተኛ
ሞተች ይላል ሰው መናኛ።

ወዮስ ለእኛ... ወዮስ ለራስ
ደረት መድቃት በእንባ መራስ
ዋርካው ሲዘ'ም አፈር መላስ።

ፍቅር የሞት መድኃኒት ልዩ ቅኔ ከቅኔያት
ስትካፈል እየኖረች፣ ስትበዛ እንድናያት፥
በረከትሽ ይደርብን
እም ሰማያት ዝናብ ሆኖ ይውረድብን።

/ዮሐንስ ሞላ/

በክብርት እናት አበበች ጎበና ሞት፣ ለቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ እና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናት ይሁን።

የሰላም እረፍት ይሁንልዎት። እናመሰግናለን።