Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም እንደምን አመሻችሁ ፤ ዛሬ በተለምዶ ጭርት (Tinea corporis) ስለሚባለው በሽታ ይዤ | ጤና ዓዳም- Tena Adam

ሰላም እንደምን አመሻችሁ ፤ ዛሬ በተለምዶ ጭርት (Tinea corporis) ስለሚባለው በሽታ ይዤላቹ ቀርቢያለሁ

ጭርት ምንድን ነው?

- ጭርት (tinea corporis) የምንለው በፈንገስ አማካኝነት የሚመጣ፣ በሁሉም የእድሜ ክልል የሚከሰት ሲሆን ከሰው ወደ ሰው፣ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ ፣ በንክኪ የሚተላለፍ የላይኛውን የቆዳ ክፍል የሚያጠቃ በሽታ ነው።

ከየት ሊይዘን ይችላል?

-በበሽታው ከተያዙ ሰዎች፣ከተለያዩ የቤት እና የዱር እንስሳቶች፣ ከአፈር ሊሆን ይችላል። በተለይ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በበሽታው የተጠቀመበትን እንደ ፎጣ፣ አልጋ ልብስ፣ ካልሲ፣ የፀጉር ማበጠሪያ በጋራ መጠቀም እና ንክኪ መፍጠር ዋነኛ መተላለፊያ መንገዶች ናቸው።

አጋላጭ ምክንያቶቹስ ምንድን ናቸው?

-ሞቃታማ እና እርጥበታማ ቦታዎች ላይ የሚኖሩ ሰዎች፣ ሰውነትን የሚያጣብቁ ልብሶችን መልበስ፣ ደካማ የበሽታ የመከላከል አቅም ያላቸው ሰዎች፣ የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች፣ ከመጠን በላይ ላብ የሚያልባቸው ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ።

ምልክቶቹስ?

-አንድ ሰው ተጋላጭ ከሆነ በዃላ ከ4-14 ቀን ምልክት ሊያሳይ ይችላል። በሰውነት ላይ ክብ ክብ የሆነ ፣ ጠርዝ ጠርዙ ቀላ ያለ (erythematous)፣ የማሳከክ ስሜት ሊኖረው የሚችል እየሰፋ የሚሄድ እንደ ቅርፊት (scaly)፣ የተሰነጠቀ (cracked) የሚመሰስል ነገር ሊወጣ ይችላል።

ምርመራዎቹስ

-የህክምና ባለሙያው በቆዳ ላይ የወጣውን ነገር አይቶ እንደ አስፈላጊነቱ ከቆዳ ላይ ናሙና በመውሰድ በቤተ ሙከራ በmicroscope በመታገዝ ፈንገስ መኖር አለመኖሩን ሊያረጋግጥ ይችላል።

የሚያመጣውስ መዘዝ?

-በተለይ ደካማ ዠበሽታ የመከላከል አቅም ያላቸው ሰዎች ለምሳሌ (HIV ህመምተኞች፣ የካንሰር ህክምና የሚወስዱ) በቶሎ በሽታውን ለማስወገድ ሊቸገሩ ይችላል።

-የሚያሳክክ፣ የተቆጣ እና የቆዳ መሰንጠቅ ሲኖር ለሌላ ባክቴሪያ ኢንፌክሽን (secondary bacterial infection) ሊጋለጡ ይችላሉ።

አእዴት መከላከል እንችላለን?

-የግል እና የአካባቢ ንፅህናን መጠበቅ

-ሰውነታችነንን ከታጠብን በዃላ በንፁህ ፎጣ ወይም ጨርቅ በደንብ ማድረቅ

-የግል መጠቀም ያልብንን ነገሮች በጋራ አለመጠቀም

-በተቻለ መጠን በዚህ በሽታ ከተበከሉ እንስሳት ንክኪ አለመፍጠር፣ በአካባቢያችን የታመሙም እንስሳት ካሉ የእንስሳት ሀኪም ጋር በመውሰድ ማሳከም ተገቢ ነው።

ህክምናውስ?

-እነደ ወጣበት ቦታ እና ስፋት የሚወሰን ሲሆን በቦታው ላይ የሚቀባ ፀረ ፈንገስ ወይም የሚዋጥ ፀረ ፈንገስ በሀኪም ሊታዘዝ ይችላል።


ዶ/ር ኤርሚያስ ማሞ