Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ ምን ገጠመኝ መሰላችሁ : የሁለቱ አመት ህፃን ልጅ ናት:: ለሰባት ቀናት በአፍ በአፍንጫዋ ደም | ጤና ዓዳም- Tena Adam

ዛሬ ምን ገጠመኝ መሰላችሁ : የሁለቱ አመት ህፃን ልጅ ናት:: ለሰባት ቀናት በአፍ በአፍንጫዋ ደም ትተፋለች እንዲሁም በሰገራም የጦቀረ ደም እንደሚወጣ ነገሩን።
.
ህፃን እንደ ወረቀት ነጭ የሆነች ስትሆን። እኛም ለምን ሰባት ቀናት ቆያቹ ስንላቸው ይቆማል በራሱ ብለን አሉ። ቀጥለንም ወዲያው የመጠጥ ውህ ምን እንደሚጠቀሙ ስንጠይቅ የምንጭ ውሃ እንደሆነ እና ምንም አይነት የማጣሪያ መንገድ እንደማይጠቀሙ ነገሩን።
.
ወድያው አልቅጥ ይሆናል ብለን የቀዶ ህክምና ካማከርን በኃላ ወዲያው ወደ ህክምና ወስደው ሲመለከቱ ትልቅ አልቅጥ ከተለጠፈበት አወጡ። ቀጥሎም ብዙ ደም ስለፈሰሳት የታካሚዋ የደም አይነት ተፈልጎ ተሰጣት ።ፈጣሪ ይመስገን ታካሚዋም ተረፈች እኔም ለምን ትንሽ ስለ አልቅጥ ትል ትንሽ ጀባ አልላችሁም።
.
leech ወይም አልቅጥ በውሃ ወስጥ የሚኖር የትል አይነት ሲሆን፡፡ ከሌሎቹ ተመሳሳይ የውሃ ትሎች የሚለዩት ባህሪዎች የፊት እና የኋላ መጣጭ ጥርሶች ሲኖሩት ፣ የተከፋፈለ የአካል ክፍሎቹ ሲኖሩት የሰውነት ጡንቻዎቹ በቀላሉ እንዲለጠጥ እና ማንኛውንው የሰው ወይም የእንስሳ አካል ላይ ተጣብቆ ደም እነዲጠጣ ይረደዋል። ህይ አልቅጥ ለማደግ እና ለመራባት የእንስሳት ደም ይፈልጋል ።
.
አልቅጥ ትል በየትኞቹ ውሃ ውስጥ ይገኛል?
.
በተለምዶ በሐይቆች ፣ በኩሬዎች ፣ በምንጮች ፣ በትንሽ ጅረቶች እና በኩሬዎች ውስጥ ይገኛሉ ።
.
እንዴት እንስሳትን ወይም ሰውን ይይዛል?
.
በአብዛኛው ጊዜ በአልቅጥ የተበከለ ውሃ ከብቶች በሚጠጡበት ጊዜ :እንዲሁም ልጆች አልቂጥ ባለበት ውሃ ሲዋኙ ወይም ሲያልፋ በተጨማሪ ውሃ ሳያጣሩ አልቅጥ ያለው ውሃ ለመጠጥነት በሚጠቀሙ ቤተሰቦች ላይ በዋነኛነት ይከሰታል። አልቅጦች አጋጣሚውን በሚያገኙበት ጊዜ በጠንካራ ጥርሶቻቸው ከነከሱ በኃላ የቻሉትን ደም ከመጠጡ በኃላ የሚበቃቸውን ያህል ከጠጡ በኃላ ከያዙት አካል ለይ ይወድቃሉ።
.
አልቅጥ ለህልፈት ህይወት ሊያስከትል እንደሚችል በቅጡ ያውቃሉን?
.
አልቅቶች ወድያው ካልተነቀሉ በእንስሳ ወይም በሰው ላይ ምን አይነት ገዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ?
.
የሚያስከትሉት ጉዳት በአጋጣሚ በነከሱት ቦታ የሚወሰን ቢሆንም በዋነኛነት የደም መፍሰስ ሲያስከትሉ።በአጋጣሚ ሆን በመተንፈሻ አካል ላይ ከተጣበቁ ከማድማት ባለፈ የአየር መተንፈሻ በመዝጋት ትንፋሽ አሳጥተው እስከ ህልፈተ ህይወት ሊያስከትሉ ይችላሉ።
.
አልቅጥ በጥርሳቸው ደም ከመምጣታቸው በተጨማሪ ከምራቃቸው የሚለቁት ኢንዛይም ሂሩዲን እንደ ደም ማቅለጫ መድሃኒቶች አይነት ባህሪ ስላለው ከተጣበቁት አካል ላይ ደም እንዲፈስ ሲያደርግ በአስቸኳይ አልቅጡ ካልተወገደ ብዙ ደም በማፍሰስ እንስሳቱን ወይም ሰውን
የደም ማነስ ከፋ ካለም ሾክ በማምጣት ህይወት የማሳጣት አደጋ ያመጣል ፡፡ ይህ ሂሩዲን የሚባል ኢንዛይም አልቅጡ ከተወገደ በኃለ እራሱ ለተወሰነ ጊዜ የደም መፍሰስ ሊያስከትል ይችላሉ ።
.
እንዴት መከላከል እና ማስለቀቅ ይቻላል?
.
የተጎዱ እንስሳትን በኬሚካሎች ማከም ወይም ተውሳኮቹን በእጅ በማስወገድ ወይም የhirudincidal ኬሚካሎችን በመተግበር እንዲሁም የውሃ አካላትን ከአልቅጦች ነፃ ማድረግ፡፡
.
በተጨማሪም ውሃ የማጥለያ መንገዶችን መጠቀም እንደነጠላ ባሉ እንዲሁም አፍልቶ መጠጣትን መንገዶች መጠቀም ቀላሎቹ መንገዶች ሲሆኑ።
.
ቤተሰብ ልብ ሊል የሚገባው ነገር ቢኖር አልቅጡ የሚታይ ከሆነ ሳይቆረጥ አንደ ሎሚ ባሉ ነገሮች በመጠቀም ማላቀቅ የሚችል ሲሆን። በውስጣዊ አካላት በሚሆንበት ጊዜ ለምሳሌ በአፍንጫ በመተንፈሻ አካል በአንጀት ወዘተ ከሆነ ወዲያው ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ማስወጣት እና ከፍተኛ የደም መፍሰስ ካለ ተመሳሳይ የደም አይነት ሊወስዱ ይችላሉ። አልቅጥ በአንድ አንድ ሃገራት ለባህላዊ ህክምና ይጠቀሙበታል።
.
አንብበው ሲጨርሱ ለወዳጅ ዘመድዎ በቀናነት ሼር ያድርጉት
መልካሙን ሁሉ ተመኘው

ዶ/ር መሐመድ በሽር የህፃናት ሐኪም
Via: hakimethio