Get Mystery Box with random crypto!

ሰሞንኛው ውዝግብ በታሪክ…. (ዶ/ር ዳዊት መስፍን፤ የማህፀንና ፅንስ ስኜሻሊስት) ጊዜው 1945 | ጤና ዓዳም- Tena Adam

ሰሞንኛው ውዝግብ በታሪክ….
(ዶ/ር ዳዊት መስፍን፤ የማህፀንና ፅንስ ስኜሻሊስት)

ጊዜው 1945 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ቤውላ ሃንተር ትባላለች። በትውልድ አሜሪካዊት የሎሳንጀለስ ነዋሪ ስትሆን በአለም ረጅም ጊዜ የፈጀውን እርግዝና በመያዝ ስሟ በ ታይም መፅሄት ሰፍሯል።

ቤውላ እንደ ሀኪሟ ዶ/ር ቤልዝ ገለፃ period መጨረሻ ያየችው February 10 ሲሆን እርግዝናዋ አንድ እርጉዝ ትወልዳለች ተብላ ከምትጠበቅበትን 40 ሳምንት (280 ቀን) ከ100 ቀናት በላይ በመቆየት በ 375ኛው ቀን ይህም ማለት 1 አመት ከ 10 ቀን በማሳለፍ February 21 ፔኒ ዲያና የተባለች የ3.14 ኪ.ግ. ጤናማ ሴት ልጅ መገላገሏን Time Magazine ዘግቧል።

በሀገራችንም ሰሞንኛው ውዝግብ እየፈጠረ ያለው የ18 አመት እርገዝናስ እንዴት ይሆን ብለው የጠየቁም የትዬለሌ ናቸው፤

ይህንን ጉዳይ ከሚያመጡ ነገሮች ውስጥ እንደ አበይትነት የሚጠቀሰውን የውሸት እርግዝና
(Pseudocyesis) በጥቂቱ ልላችሁ ወደድኩ…

የውሸት እርግዝና (Pseudocyesis)

ማርገዝ ለአንድ ጥንዶች ወይም ወላጆች እጅግ በጣም ደስታን የሚጭር ጊዜ ሲሆን በተለይ ደግሞ ታስቦ እና ታቅዶ የተረገዘ እርግዝና የበለጠ ይሆናል።

አንዳንድ ጊዜ ግን ሴቶች pseudocyesis (በጣም በትንሹ ደግሞ ወንዶች ላይ … Couvade syndrom የሚሰኘው) ሳያረግዙ ከብዙ ነገሮች አንፃር አርግዣለሁ ብሎ ማሰብ በታሪክ አዲስ ክስተት አይደለም።

ምን ይሆን ምክንያቱ

ባብዛኛው ጊዜ ይህ አይነት አርግዣለሁ ብሎ እራስን ማሳመን ምክንያቱ ይህ ነው መባል የማይቻም ሲሆን ነገር ግን የሚከተሉት ነገሮች እንደ መላምት ይጠቀሳሉ:-

እጅጉን ማርገዝ መፈለግ ይህ ከብዙ ነገሮች አንፃር የመጣ ፤ ለምሳሌ
ብዙ ጊዜ ለማርገዝ ሙከራ እየተደረግ እንቢ ሚላቸው ሴቶች ላይ
በተደጋጋሚ ውርጃ የሚያጋጥማቸው
ወደ ማረጥ እየቀረቡ ነገር ግን ማርገዝ የሚፈልጉ ላይ

እጅጉን ማርገዝ አለመፈለግ ነገር ግን ሁሌም አርገዣለሁ ብሎ መጠርጠር እና ማሰብ

እነኚህ ከላይ የተጠቀሱት ሁናቴዋች ወይም ስሜቶች ሴቲቱ በአካሏ ላይ የእርግዝና ምልክቶች ያሉ እንዲመስላት ያደርጋል።

በነኚህ ምልክቶች ምክንያት የሴቲቱ ጭንቅላት እርግዝና እንዳለ በማመን እርግዝና ላይ ከመጀመሪያ ጀምሮ አስተዋፅዎ ያላቸውን በጭንቅላት የሚመነጩ ንጥረ ቅመሞች እንዲመነጩ በማድረግ ትክክለኛ የሚመስሉ የእርግዝና ምልክቶች እንዲሰሟት ያደርጋል።

ሊታዩ የሚችሉ ስሜቶች

የወር አበባ የተዛባ መሆን ፤ በጣም ማነስ ወይም እስከጭራሹ አለማየት

ጡት መጨመር እና የህመም ስሜት፤ አንዳንዴም ወተት እስከማውጣት መድረስ

ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ

ሆድ እያበጠ እና እየጨመረ መምሰል

እንቅስቃሴ ያለ መምሰል እና ኪሎ መጨመር

ምጥ አለኝ ብሎ ሆስፒታል እስከ መሄድ እስከ መድረስ ሊሆኑ ይችላሉ

ሊደረጉ የሚችሉ ምርመራዎች

የእርግዝና ምርመራ:- የሽንት እርግዝና ምርመራ እርግዝና እንደሌለ ያሳያል

አልትራሳውንድ:- ምንም አይነት ፅንስ እንደሌለ ያሳያል

ህክምናውስ

⁃ ብዙን ጊዜ እርግዝና ለሚፈልግ እና በጣም ለጓጓች ሴት እርግዝና የለሽም ማለት በጣም የሚያበሳጭ ነገር ስለሚሆን በተቻለ አቅም ስላለው ሁኔታ ተረጋግቶ እና አረጋግቶ መንገር ተገቢ ነው።

⁃ ቢቻል በስነልቦና ሀኪም ቢነገራቸው እና ቀጣይ ያሉ ክትትሎች ቢያደርጉ ይመከራል።