Get Mystery Box with random crypto!

​​ ቪፒኤን ለምን እንጠቀማለን? ጥቅሙስ ምንድን ነው? ቪፒኤን (VPN) የኢንተርኔት ግንኙነታች | ኢትዮ ቴክኖሎጂ ( Ethio technology )

​​ ቪፒኤን ለምን እንጠቀማለን? ጥቅሙስ ምንድን ነው?

ቪፒኤን (VPN) የኢንተርኔት ግንኙነታችንን ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን እና የምንለዋወጣቸዉ መረጃዎች ከመረጃ #በርባሪዎች ጥቃት የተጠበቁ እንዲሆኑ የሚረዳ #ሶፍትዌር ነው፡፡

ተጠቃሚዎች የቪፒኤን ግንኙነት ሲፈጥሩ ደህንነቱ የተረጋገጠ የመረጃ መተላለፊያ መንገድ ይፈጥራሉ፡፡
#ቪፒኤን በተለየ ማስተላለፊያ መንገድ የሚተላለፉ ዳታዎችን ሚስጥራዊ የሚያደርግ በመሆኑ #ማንኛዉም የመረጃ በርባሪ የመረጃዉን ይዘት ማዎቅ እንዳይችል ከማድረጉ ባሻገር የመረጃ ግንኙነቱ የሚሆነዉ #በሁለቱ ባለመብት(ባለፍቃድ) አካላት ብቻ ነዉ፡፡

ሶፍትዌሩ የቀጥታ የበይነ-መረብ ግንኙነት 'የኦንላይን' እንቅስቃሴ በመደበቅ እንዲሁም እንዳይታይ በማድረግ(የትኛዉን ድረ-ገጽ እንደጎበኘን እና ምን አይነት ዳታዎችን እያስተላለፍን መሆኑን) ባለማሳዎቅ ያግዘናል፡፡

ይህን አገልግሎት በተገቢው መንገድ ማግኘት የምንችለው ደግሞ የቪፒኤን ሶፍትዌር ደንበኛ በመሆን አገልግሎቱን መጠቀም ስንጀምር ነዉ፡፡

ደንበኛ በመሆናችን የምናስተላልፋቸዉ ዳታዎች ከመዳረሻዉ ኔትወርክ ከመድረሳቸዉ በፊት #ይመሰጠራሉ፡፡

ቪፒኤንን ለምን መጠቀም አስፈለገ?

ማንኛዉንም የዌብ ተግባራት #ኢንክሪፕትድ(የተመሰጠሩ) እንዲሆኑ ያደርጋል።

የቀጥታ የበይነመረብ ግንኙነት (online) ተግባራችንን #በመደበቅ ከሚከታተሉን የመረጃ መንታፊዎች ያድነናል፡፡

መዳረሻችንን በግልፅ እንዳይታይ እንዲሁም በቦታ የተገደቡ ዌቦችና ይዘቶችን አገልግሎት ማግኘት እንድንችል ይረዳናል።

በዌብ(በይነ-መረብ) ተግባር ላይ የማንነት መታዎቅ አጋጣሚን በእጅጉ ያጠባል።

የህዝብ ዋይፋይ ሆትስፖቶችን በምንጠቀምበት ጊዜ ግንኙነቱ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ያደርግልናል፡፡

በአጠቃላይ ደህንነቱ የተጠበቀ መረጃና የመረጃ ልዉዉጥ መንገድ ይፈጠርልናል ማለት ይቻላል፡፡