Get Mystery Box with random crypto!

ሰላማችሁ ይብዛ ውድ የሀገሬ ልጆች የቻናሌ ቤተሰቦች እንደምን አመሻችሁ እኔሬ ስለአንዳንድ ነገሮች | 🇪🇹 ኢትዮ Students

ሰላማችሁ ይብዛ ውድ የሀገሬ ልጆች የቻናሌ ቤተሰቦች እንደምን አመሻችሁ እኔሬ ስለአንዳንድ ነገሮች እንድንወያይ ነበር!
እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ሰው ይወለዳል ፣ ይማራል ፣ ይመረቃል ፣ ስራ ያጣል ፣ ከዛ የሆነ ስራ ካገኘ እንኳን ተቀጥሮ ይሰራል ፣ Normal የተለመደ ኑሮ በ5000 ብር ደሞዝ ይኖራል ከዛ ይሞታል Fact ነው።

እና ብዙዎቻችን Almost 80% የምንሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ የህይወታችን መሰረት ትምህርት ቤት ገብቶ መማር ብቻ መስሎ ይታየናል። ዛሬ ላካፍላችሁ የፈለኩት ፍላጎቱ ካለን ፣ ብርታቱ ካለን ፣ አጋጣሚዎች ከተመቻቹልን የተሻለ ነገር እንሰራለን።

ለምሳሌ ህንዶችን እንመልከት። ከተራ መቃብር ቆፋሪ እስከ አውሮፕላን አብራሪ ዩቱዩበር ናቸው። ብዙዎቹ ገንዘብ የሚያገኙት ከተለያዩ የኦንላይን ስራዎች ነው። በዛም አያቆሙም እኮ፡ የተለያዩ የOnline ኮርሶችን ይወስዳሉ ፡ ይቀጠራሉ። ከGoogle.com ስራ አስኪያጅ ብንጀምር ብዙዎች Google ላይ ያሉ ሰዎች ህንዳዊያን ናቸው። ብዙዎቹ Google በየአመቱ ከሚቀጥራቸው ሰዎች ውስጥ ከግማሽ በላዩ ኮሌጅ ያልገቡ ናቸው! Microsoft ከ65% በላይ ተቀጣሪዎች ከህንድና ከAsia ካሉ ሀገራት ነው። እንደውም የሆነ ጊዜ የMicrosoft ፈጣሪውና ባለሀብቱ ቢል ጌትስ " ከግማሽ በላይ ሰራተኞችህ ህንዳዊያን ናቸው ለምንድነው እዚህ አሜሪካ አምጥተህ የቀጠርካቸው? " ተብሎ ሲጠየቅ ምን ብሎ ቢመልስ ጥሩ ነው? " ምክንያቱም ህንድ ውስጥ ሌላ Microsoft እንዳይፈጥሩ " ብሎ መልሷል። ይህ የሚያሳየው ምን መሰላችሁ Lecture ማጥናት ብቻ ሳይሆን ያጠናነውን ነገር በጥሩ ብቃት መስራትና መፍጠር መቻል አለብን!

የሚገርማችሁ ባለፈው $200,000 የተሸጠ የኢትዮጵያ NFT አይቼ ገርሞኝ ሳልጨርስ ... ለአንድ ድርጅት የስልክ አፕ ለመስራት ከ35,000 ብር ጀምሮ መሆኑን እና  ዌብሳይት ለመስራት ደግሞ በትንሹ ከ 7000 ብር ጀምሮ መሆኑን አየሁ ኢትዮጵያውያን Ethical ሀከሮች በBug Buntyነት እየሰሩ በወር እስከ $7500 እንደሚሰሩ ሰማሁ! ከዛ ምን ጉድ ነው ብዬ ሳልጨርስ የዩቲዩበሮችን ገቢ ለማጣራት ሞከርኩና የዳሎል ኢንተርቴይመንት ቻናል የወር ገቢ በትንሹ 100,000 ብር እንደሆነ ሰማሁ! እና እነዚህን ነገሮች ሁሉ ትምህርት ቤት ተምረው ነው?

ምን ለማለት ፈልጌ ነው! ግዴታ ዩኒቨርሲቲ ገብተን በዲግሪ የመመረቅ ግዴታ የለብንም! አላማው ገንዘብ የማግኘት ነው! ይዞ መገኘት! ይህንን ስል ማንንም ተስፋ ለማስቆረጥ አይደለም ማንንም ደግሞ Over inspire ለማድረግ አይደለም። እውነታውና ሀቁ ግን ይሄ ነው። intelligent, Creative, Hard Worker ሆነህ እስከተገኘህ ድረስ አንተ ሁሉም ተፈላጊ ነህ


ሼር በማድረግ ወደዚህ ቻናል ሰዎችን ብትጋብዙ ደስ ይለኛል



Yohana

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS