Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር የአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፈተና አሰጣጥን በተመለከ ትላንት ሰኞ ምሽት ከፕሬዚ | 🇪🇹 ኢትዮ Students

ትምህርት ሚኒስቴር የአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፈተና አሰጣጥን በተመለከ ትላንት ሰኞ ምሽት ከፕሬዚደንቶችና የተቋማት ሃላፊዎች ጋር ከተወያየ በኃላ ከፈተናው ጋር በተያያዘ ውሳኔ ማስተላለፉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሚመለከተው አካል ለማወቅ ችሏል።

በዚሁ የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ የሬሜዲያል ፈተና አሰጣጥ በሚከተለው መልኩ እንዲከናወን ተወስኗል።

- በ26/10/2015 የተሰጡት የሬሜዲያል ፕርግራም ፈተናዎች #ተሰርዘው ተማሪዎች በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ እንዲደረግ ተወስኗል።

- ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ #ካምፓስ ያላቸውን #የግል_ከፍተኛ_ትምህርት ተቋማት ፈተና  ወደ ፊት ቀርቦ በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም  እንዲሰጥ እንዲደረግ ተወስኗል።

- በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑትን ተማሪዎች ፈተና መስጠቱን ወደ መስከረም ወር ማስተላለፉ በተማሪዎችና በተቋማት ላይ የሚያሳድረውን ጫና ከግምት በማስገባት የተዘጋጁትን ፈተናዎች በመለወጥ ፈተናዎች ኢንክሪፕትድ ሆነው ለዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንቶች ደርሰው እንዲባዙና ሁሉም ፈተናዎች በተመሳሳይ ጊዜ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ እንዲሰጡ እንዲደረግ።

- የፈተና ጥያቄዎች ለዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንቶች ከመድሳቸው በፊት ተማሪዎች #ከቀኑ_6 ሰዓት ላይ ተፈትሸው ወደ መፈተኛ አዳራሽ ገብተው ፈተናውን እንዲጠባበቁ በማድረግ እንዲፈፀም ውሳኔ ተላልፏል።

ተቋማት ከትምህርት ሚኒስቴር በተላከላቸው ውሳኔ መሰረት ተማሪዎቻቸው #ከቀኑ_6 ሰዓት ተፈትሸው ወደመፈተኛ ክፍል ገብተው ፈተናውን እንዲጠባበቁ መልዕክት እያስተላለፉ እንደሚገኙ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከየተቋማቱ የደረሰው መልዕክት ያስረዳል።