Get Mystery Box with random crypto!

የህግ ጉዳዮች/Dhimma Seeraa

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioseeraa — የህግ ጉዳዮች/Dhimma Seeraa
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioseeraa — የህግ ጉዳዮች/Dhimma Seeraa
የሰርጥ አድራሻ: @ethioseeraa
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 772
የሰርጥ መግለጫ

ሰለሞን ምስጋናው አብዲሳ
በፌዴራልና በኦሮሚያ ክልል ማናቸው ፍ/ቤት
ጠበቃና የህግ አማካሪ
Abukaaattoo fi Gorsaa Seeraa
Legal Consultant and Attorney

251911592762
AM Here to Serve JUSTICE

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-10 16:39:54 #የቀበሌ_ቤት_ለሶስተኛወገን_ስለማስተላለፍ

የቀበሌ ቤትን የተከራየ ማንኛውም ሰው በሞት ሲለይ ወይም ከአካባቢው በተለያየ ምክንያት ሲለቅ ቤቱን ለቤቶችና አስተዳደር ቢሮ እንዲመልስ ይደረጋል።ሆኖም ሟች በተከራየው ቤት ውስጥ የሚከተሉት ፦
1/ የተከራይ ሚስት ወይም ባል ስለመሆናቸው ሕጋዊ የጋብቻ ማስረጃ ሲቀርብ ቤቱን መረከብ ይችላል ።

2/ የተከራይ ልጆችና በሕጋዊ መንገድ በጉዲፈቻ ያደጉ ልጆች በቤቱ ውስጥ እየኖሩ ስለመሆናቸው በወረዳው ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ሲረጋገጥ ቤቱን የሚረከቡ ይሆናል።

3/ ዕድሚያቸው ከ18 ዓመት በታች ሆነው በቤት ውስጥ መኖር የጀመሩና ሟች እስከሞተበት ቀን ድረስ ቤት ውስጥ ከወላጆቻቸው ተለይተው እንደ ልጅ መኖራቸው በወረዳው የቤተሰብ አባላት መመዝገቢያ ቅፅ ውስጥ መመዝገቡ ሲረጋገጥ ቤቱን የሚረከቡ ይሆናል።

4/ በችግር ምክንያት ከተከራይ ጋር በጥገኝነት የሚኖር የባል ወይም የሚስት እናት ወይም አባት ስለመሆናቸው በቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ሲረጋገጥ ቤቱን ሊረከቡ ይችላሉ።

5/ ከላይ ከ 1-4 የተገለፁት ሁሉ ወራሾች ስለመሆናቸውና በስማቸው ወይም በትዳር አጋራቸው ስም የጋራ መኖሪያ ቤት፣የግል መኖሪያ ቤት ፣የቤት መስሪያ ቦታ ከመንግሥት የተከራዩት ቤት የሌላቸው ወይም ከ1997 ዓ.ም ቡኃላ ቤት በሽያጭ ወይም በስጦታ ያላስተላለፋ መሆኑ በማስረጃ ሲረጋገጥ ቤቱን በቀድሞ ኪራይ ተመን መሠረት በአዲስ ውል እንዲከራዩ እነዚህ ሰዋች ይፈቀድላቸዋል ማለት ነው ።
ተከራይሚስትለባልንጀራው፣ለልጅ፣ለሞግዚት፣የኪራይ ውል በስሙ እንዲያድሱለት ህጋዊ ውክልና መስጠት ይችላል።ነገር ግን ተከራይ ከነዚህ አካላት ውጪ ለሌላ ወገን በውክልና ስም ቤቱን አስተላልፎ አምስት አመትና ከዚያ በላይ በቤት ውስጥ ካልኖረ የቤት ኪራይ ውል እንዲቋረጥ በማድረግ መንግስት ቤቱን ይረከባል ማለት ነው።ይህም የመንግስት ቤቶች አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 5/2011 ላይ በግልፅ ተደንግጎ ይገኛል።
55 views13:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 16:37:08 40/60
ባለ ሶስት መኝታ ለተመዘገባቹ...ዕጣ የወጣላቸው ዝርዝር...
52 viewsedited  13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 16:35:08 40/60
ባለ ሁለት መኝታ ለተመዘገባቹ...ዕጣ የወጣላቸው ዝርዝር...
53 viewsedited  13:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 11:15:41 DASHEN BANK IS LOOKING FOR FRESH GRADUATES

Legal Officer

Job Description:

Get-As International PLC would like to invite qualified and experienced candidates for the following position.

Term of employment:Permanent

Job Requirements:

Requirement    

BA/ Degree in LLB from recognized University 

Experience 

1 year work experience in legal service

Working in private company is more advantageous 

How To Apply:

Interested applicants are invited to submit in person their non-returnable application, with CV and copies of relevant documents within 5 days from the first date of this announcement in person.

Address: Get-As International PLC, head office 2nd floor Arada Sub-City around commercial Printing Press, in front Ministry of Innovation and Technology or email address gizachewadmsasu12@gmail.com /for email users send only application letter and updated CV/

Tel No. 011-1559543,  011 1571309,  011-1557485

Posted: 07.06.2022

Deadline: 07.11.2022

 Job Category: Legal
Salary: Negotiable
Location: Addis Ababa
94 views08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 14:08:51
150 views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 09:09:20 ረግ እንደሚገባ ያስቀምጣል፡፡ ስለዚህ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 50(2) ስያሜን ይጨምራል ብንል እንኳ፤ አባት እና እናት መስማማት ካቃታቸው ምን ሊደረግ እነደሚገባ ሊያስቀምጥ ይገባ ነበር፡፡ በመሆኑም ከላይ የተጠቀሰው ድንጋጌ የመፍትሄ ሀሳብ አለማስቀመጡ ስያሜን እንደማያካትት ገላጭ ማስረጃ ነው፡፡

የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ መሰረት በአንዳንድ ልዩ በሆኑ ሆኔታዎች እናት እና አባት በህይወት እያሉ የአሳዳጊነት መብት ለሌላ ሦስተኛ ወገን ተላልፎ ሊሰጥ የሚችልባቸው ሁኔታዎች አሉ፡፡ ስለዚህ በአሳዳጊነት ‹Guardian & Tutor› መብት ውስጥ ስያሜ መስጠት ከተካተተ ለሦስተኛ ወገኖች መብቱ ሊተላለፍ ሊሆን ነው ማለት ነው፡፡

አንድ ሕግ ከሚሻርባቸው መንገዶች መካከል በሌላ ሕግ መውጣት ምክንያት እና ጥቅም ላይ ባለመዋል(ባለመጠቀም) ይገኙበታል፡፡ በመሆኑም የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ በስራ ላይ ሲውል ሊሽር የሚገባው በፍትሐብሔር ሕጉ ስር የነበሩትን ስለ ቤተሰብ የሚደነግጉ አንቀፆች እንጂ ስለግል ሕግ ‹Law of Person› አንቀፆችን ሊሆን አይገባም፡፡ እንዲያውም ጥቅም ላይ ባለመዋላቸው የተነሳ ስለ የቤተዘመድ ስም ‹Family Name› የሚያትቱት አንቀፆች ተሻሩ እንጂ እንኳን ለልጁ ቅድሚያ ስም ማውጣት ይቅርና ሚስት ራሷ የአባቷን ስም እንድትቀይር ልትገደድ ትችል ነበር፡፡



በመሆኑም ስም የማውጣት መብት ለአባት ቅድሚያ መስጠቱ እኩልነትን አይፃረርም፡፡ ምክንያቱም የፆታ እኩልነት ማለት በሁሉም ረገድ እኩል ይሁኑ ማለት ሳይሆን እንደ ሁኔታው አንዱ ሌላው ላይ ጫና እንዳያሳድር ለመጠበቅ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ለሴቶች ከህገ-መንግሥቱ ጀምሮ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ እና ሌሎች ሕጎች ቅድሚያና ልዩ ጥበቃ ያደርጋሉ፡፡ ስለዚህ ለልጅ ስያሜ ቅድሚያ የመስጠት መብት በፍትሐብሔር ሕጉ ስር እንደተቀመው የአባት ነው፡፡

ማጠቃለያ

በእውነቱ ከሆነ ከላይ የተጠቀሱት የሕግ ባለሙያዎች ክርክር እንዳለ ቢሆንም በተግባር ስም እኔ ላውጣ በሚል ወደ ፍ/ቤት ያመራ መዝገብ ወይም የሰበር ውሳኔ እስከአሁን ያለ አይመስለኝም(በግሌ አላጋጠመኝም)፡፡ በተጨማሪም የማህበረሰባችን የቤተሰብ አወቃቀር እና የቤተሰባዊነት መርህ እንደሚያሳየው አንድ ህፃን ልጅ ሲወለድ በብዛት ስም የሚያወጡት ከወላጆቹ ይልቅ ጓደኛ፣ ጎረቤት እና ዘመድ አዝማድ የመሳሰሉ ሰዎች በመሆናቸው ስያሜ ላይ ብዙም ግጭት አይስተዋልም፡፡ ቢያጋጥምም ልጅ ማግኘት ትልቅ የደስታ ምልክት ስለሆነ እዛው  በቤተሰቡ ውስጥ የይፈታል እንጂ ወደ ፍ/ቤት የመምጣት ዕድሉ ጠባብ ነው፡፡

ነገር ግን እንደሕግ ባለሙያ ወጥ የሆነ አካሄድ ሊኖር ስለሚገባ እና ጉዳዩ ወደ ፍ/ቤት ቢመጣ እንኳ የተለያየ ውሳኔ እንዳይኖር በሚል ይህን ክርክር ለማሳወቅና ግልፅ ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ ፅሁፍ ነው፡፡ በመሆኑም እንደ ገለልተኛ ባለሙያ ስመለከተው ሁለቱም ጎራዎች ተገቢ የሆነ የክርክር ነጥብ አላቸው፡፡ የመጀመሪያው ጎራ የፍትሐብሔሩ የስያሜ አንቀፆች ከፆታዊ እኩልነት ጋር መጋጨታቸው እውን ነው፤ በሌላኛው ጎራ ደግሞ በግልፅ ያልተሻረ ሕግ እያለ በሌላ ሕግ መገዛት ተገቢ አለመሆኑ እና አንድን አንቀጽ ከታለመለት አላማ ውጪ መለጠጥ ከመሰረታዊ የሕግ መርሆች አንፃር የሚፃረር መሆኑ እውነት ነው፡፡ ከዚህ አንፃር የኔ እይታ፤ ምንም እንኳ ሕጉ እኩልነት የሚያጠነጥን ባይሆንም በግልፅ እስካልተሻረ ድረስ በደፈናው መሸፋፈን የለብንም፡፡ ስለዚህ የትኛው ሀሳብ ሚዛን ይደፋል የሚለው ለአንባቢዎች፤

‹ፍርዱን ለናንተው ብያለሁ›

Read 301 timesLast modified on Jun 27 2022




Tagged under ስም ስያሜ name family law choicefirstname

አቤል ልዑልሰገድ አበበ
The blogger is currently working as an Assistant Lecturer in Dire Dawa University. You may reach him by his email at wizyabel21@gmail.com

 

LATEST FROM አቤል ልዑልሰገድ አበበ
ጋብቻ ሳይፈፀም እንደባልና ሚስት አብሮ መኖር፤ አንድምታዎቹ እና ተግዳሮቶቹ
ቀለብ የመስጠጥ ግዴታ ፅንሰ ሀሳብ በተሻሻለው የኢትዮጵያ የቤተሰብ ሕግ
ስምና ድንጋጌዎቹ በኢትዮጵያ የፍትሐብሔር ሕግ
ሳይፋቱ ፍቺ በተሻሻለው የኢትዮጵያ የቤተሰብ ሕግ
RELATED ITEMS
Ilmi Maqaan Abbaa Isaa akka jijjiirramuuf kallattiidhaan gaafachuu ni danda’aa?
ጋብቻ በሚፈርስበት ወቅት የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ሥነ-ሥርዓት ከሰበር ውሳኔዎች ጋር ተገናዝቦ የቀረበ
ጋብቻ ሳይፈፀም እንደባልና ሚስት አብሮ መኖር፤ አንድምታዎቹ እና ተግዳሮቶቹ
ቀለብ የመስጠጥ ግዴታ ፅንሰ ሀሳብ በተሻሻለው የኢትዮጵያ የቤተሰብ ሕግ
ሳይፋቱ ፍቺ በተሻሻለው የኢትዮጵያ የቤተሰብ ሕግ
You are here:  HomeBlog PostsFamily Law Blogአዲስ ለተወለደ ህፃን ልጅ ስም የማውጣት መብት፤ የእናት ወይስ የአባት? - የሕግ ባለሙያዎች ወግ
^Top
212 views06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 09:09:20 Abyssinia Law
LOGIN

FAMILY LAW BLOG
አዲስ ለተወለደ ህፃን ልጅ ስም የማውጣት መብት፤ የእናት ወይስ የአባት? - የሕግ ባለሙያዎች ወግ
አቤል ልዑልሰገድ አበበ Jun 27 2022
Print Email
 

መግቢያ

ከሰሞኑ በአንድ ጠበቆች፣ ዳኞች፣ ዓቃቢያነ ሕግች፣ የሕግ ምሁራን እና የሴቶች መብት አቀንቃኞች የተገኙበት የሴቶች እኩልነት እና ሰብዓዊ መብቶች በሚል ርእስ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ተገኝቼ ሳለሁ፤ አንዲት ተሳታፊ ጠበቂት ሃሳቧን ስታጋራ ለህፃን ስያሜ የመስጠት መብት የወላጆች የጋራ መብት ነው ብላ በደፈናው ተናግራ ስትጨርስ የውይይቱ መሪ ይህን ሀሳብ በሕግ የተደነገገ መብት ነው ብላ ስትደግም ከተሳታፊዎች ጉርምምታ ሲበዛ ለምን አላጠራውም በሚል፤ ይህንን ንግግሯን የሚደግፍ የሕግ ማዕቀፍ ካለ በሚል ጥያቄ አቅርቤላት ነበር፡፡ አወያዪዋም የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ እና ሕገ-መንግሥቱ ይደነግጋል በማለት ምላሽ ስትሰጥ፤ በዚህ ነጥብ ላይ የጦፈ ክርክር ይነሳል፡፡

በአንድ ወገን ይህንን ስያሜ የመስጠት ቅድሚያ መብት የሚደነግገው የፍትሐብሔር ሕጉ ነው እንዲሁም በቤተሰብ ሕጉ በግልፅ የተደነገገ አንቀጽ የለም በሚል ሲቃወሙ፤ በሌላ ፀንፍ አወያዩዋን ጨምሮ ሌሎች ተሳታፊዎች ደግሞ የሴቶች እኩልነት በሕገ-መንግሥቱ ስለተደነገገ እና በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ስር ቤተሰብን በጋራ የማስተዳደር ኃላፊነት በጋራ መሆን አለበት በሚለው አንቀጽ ስር ይወድቃል በማለት ተከራከሩ፡፡ በመጨረሻም ከስምምነት መድረስ ሲያቅተን ጭብጥ ቀይረን ውይይቱን ቀጠልን፤ ነገር ግን እንደ አንድ የሕግ ባለሙያ ጉዳዩን የበለጠ ልመረምር ይገባል ብዬ ይህንን ዕልባት ያላገኘ ነጥብ ወደ ማውቃቸው የሕግ ምሁራን ወስጄ ሀሳባቸውን ስጠይቅ እዚህም ሁለት ጎራ የያዘ ምላሽ አገኘሁ፡፡ በዚህም የተነሳ ይህንን ነጥብ የበለጠ ለማጥራት ከሕግ ማዕቀፎቹ፣ ከመሰረታዊ የሕግ ፍልስፍና መርሆች እና ከፆታ እኩልነት አንጻር ለመመርመር ወደድኩ፡፡ ምንም እንኳ በውይይቱ አንዱን ጎራ ይዤ ስከራከር የነበረ ቢሆንም ለዚህ ፅሁፍ አላማ ሲባል ገለልተኛ ሆኜ የሁለቱንም ገራ ክርክር አካትቼ እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡  

በመሰረቱ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ከመምጣቱ በፊት ቤተሰብን በሚመለከት ገዥ ድንጋጌዎችን በስሩ አቅፎ የነበረው የፍትሐብሔር ሕጉ ነበር፡፡ የፍትሐብሔር ሕጉም በንጉሱ ዘመን እንደመውጣቱ ወንድን ከሴት ከፍ ያደረጉ ሕግጋትን በውስጡ አቅፎ ይዟል፡፡ ለምሳሌ በቤተሰብ አምዱ አባት የቤተሰብ ራስ መሆኑን እንዲሁም ቤተሰቡ የት እና በምን ሁኔታ መኖር እንዳለበት የመወሰን መብት የመሳሰሉት አቅፎ ይዟል፡፡

ከመንግሥት ለውጥ ጋር ተያይዞ አሁን የምንጠቀምበት ሕገ-መንግሥት ዴሞክራሲን አስተዋውቆ የጾታ እኩልነትን ሲያውጅ፤ ከዚህ ጋር የማይሄዱ ሕጎች የቤተሰብ ሕጉን ጨምሮ ተሻሽለዋል፡፡ በዚህም አግባብ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ወንድ እና ሴት በትዳር ውስጥ አብረው ሲኖሩ በግላዊም ሆነ በንብረት ላይ እኩል መብት እንደሚኖራቸው ይደነግጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከትዳር መፍረስ በኋላም በልጆች አሳዳጊነት እና ንብረት ክፍፍል ላይ እኩል መብት አላቸው በማለት ያትታል፡፡ ይህ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ በስራ ላይ ሲውል ከዚህ ቀደም እንጠቀምበት የነበረውን የፍትሐብሔር ሕጉ ውስጥ የነበረውን የቤተሰብ ሕግ ድንጋጌውች በሙሉ ሽሯል፡፡



በሌላ በኩል ስለ አንድ ሰው ስያሜ እና ተያያዥ ጉዳዮች (Law of Person) የሚያስተዳድሩት ድንጋጌዎች በፍትሐብሔር ሕጉ ከአንቀጽ አንድ ጀምሮ ይገኛሉ፡፡ በዚሁ ሕግ አንቀጽ 34-35 መሰረት ለአንድ ህፃን ልጅ ስያሜ የመስጠት መብት ቅድሚያ ለአባት መሆኑን ያትታል፡፡ በተጨማሪም አባት ሳይኖር የአባት ቤተሰቦች፣ ከሌሉ እናት እና የእናት ቤተሰቦች እያለ ቅደም ተከተሉን ያስቀምጣል፤ በዚሁ ሕግ እናት ለልጁ በተለምዶ የቤት ስም የማውጣት መብት ተሰጥጧታል፡፡ ይህ ስለ ሰዎች ግላዊ ሁናቴ የሚደነግገው ሕግ ስለ ቤተዘመድ ስም ያስቀመጣቸው አንቀፆች ጥቅም ላይ ካለመዋላቸው የተነሳ ተሸረዋል፤ ከነኚህ ስለ ቤተዘመድ ከሚያትቱት አንቀፆች ውቺ ያሉት ድንጋጌዎች ግን በስራ ላይ የሚገኙ ገዢ ሕግጋት ናቸው፡፡

አሁን ለዚህ ፅሁፍ መነሻ ወደሆነው የክርክር ነጥብ ስመለስ፤ በመጀመሪያ ስያሜ የመስጠት መብት የጋራ መብት ነው ከሚሉት ወገኖች መከራከሪያ ጭብጦችን ልዘርዝር፤

የፆታ እኩልነት በህገ-መንግሥት አንቀጽ 7፣ 25፣ 35 መሰረት እና በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 50፣ 54፣ና 66(1) ስር በመቀመጡ፤ ይህንን ሚቃረኑ ሕጎች ውጤት አልባ ናቸው፡፡ ስለዚህም ስለ ስያሜ በሚደነግገው የፍትሐብሔር ሕግ ስር ለአባት ስያሜ የመስጠት ቅድሚያ የሚሰጠው አንቀጽ ውጤት አልባ ይሆናል፡፡



ለአንድ ሕፃን ልጅ ስያሜ የመስጠት ጉዳይን የሚመለከተው ሕግ የፍትሐብሔር ሕጉ ሳይሆን የቤተሰብ ሕጉ ነው፡፡ ምክንያቱም ጉዳዩ ከልጅ ስያሜ ባለፈ እናትን እና አባት ስለሚያካትት የግል ሳይሆን የቤተሰብ ጉዳይ ስለሚሆን በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ስር ሊካተት ይገባል፡፡

የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ይህንን የስያሜ ጉዳይ በተመለከተ በቀጥታ የተቀመጠ አንቀጽ ባይኖረውም፤ ቤተሰብን በጋራ ስለማስተዳደር የሚያትተው አንቀጽ 50(2) እንደሚያዘው ‹ባልና ሚስት በማናቸውም ሁኔታ በጋራ ተባብረው የቤተሰባቸውን ጥቅም ማስከበርና ጥበቃ የማድረግ፤ በተጨማሪም ልጆቻቸው ኃላፊነት የሚሰማቸው ዜጎች እንዲሆኑ ለማስቻል በጥሩ ትምህርት እና እንክብካቤ ሊያሳድጉ ይገባል›፡፡ በመሆኑም እናትና አባት ለልጆቻቸው አሳዳጊና ተንከባካቢ ‹Guardian & Tutor› ስለሆኑ ይህ ሀላፊነታቸው ደግሞ በተዘዋዋሪ ‹Impliedly› ስያሜ መስጠትን ያካትታል፡፡ ስለዚህ አንቀጽ 50(2) በቀጥታ ባይገልፀውም ተለጥቶ ሲነበብ ስያሜ መስጠትንም የሚጨምር ይሆናል፡፡

ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች የተነሳ የፍትሐብሔር ሕጉ የስያሜ ድንጋጌዎች ከፆታዊ እኩልነት መብት ጋር ተፃራሪ ስለሆነ ሊሻር እነደሚገባው፣ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 50(2) በቀጥታ ባይገልፀውም ተለጥቶ ሲነበብ ስያሜ መስጠትንም የሚጨምር ስለሆነ እና ጉዳዩ ከሚያካትታቸው ሰዎች አንፃር ከግላዊ ባህሪ ይልቅ ቤተሰብን የሚመለከት ስለሆነ ስያሜ የመስጠት መብት በሁለቱም ተጋቢዎች የጋራ ስምምነት መሰረት የሚከናወን ይሆናል በሚል ተከራክረዋል፡፡



በሌላ በኩል የዚህ ሀሳብ ተቃራኒዎች በበኩላቸው የሚከተሉትን መከራከሪያ ነጥቦች በማስቀመጥ ስያሜ የመስጠት መብት በፍትሐብሔር ሕጉ ድንጋጌ መሰረት ቅድሚያ የአባት ነው በማለት ተከራክረዋል፤

በመጀመሪያ ጉዳዩ የአንድን ሰው ስያሜን የሚመለከት ስለሆነ የግል ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም ስም ለልጁ መጠሪያ እስከሆነ ድረስ የቤተሰብ ሕግ ገዢ ሊሆን አይችልም፡፡ በፍትሐብሔር ሕጉ በግልፅ ስለ ስያሜ የተደነገጉ ድንጋጌዎች እያሉ በተውሶ ከሌላ ሕግ መጠቀም ከሕግ ፍልስፍና አንፃር ተገቢ አይደለም፡፡

ሀገራችን የምትከተለው የሕግ ስርዓት ‹Civil Law Legal System› በመፅሀፍ የተደነገጉ ሕጎች ስለሚጠቀም አንቀፆች በግልፅ ለታለመላቸው አላማ ብቻ ነው ሊውሉ የሚገባው፡፡ በመሆኑም የህገ-መንግሥቱ የእኩልነት ድንጋጌዎች እና የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 50(2) በልኩ ሊተረጉመው ይገባል እንጂ የሕግ ስርዓታችን በማይፈቅድ መልኩ እነደ አውሮፓና አሜሪካ ሀገራት ሊለጠጥ አይገባም፡፡

በተያያዘም አንድ ሕግ አንድን ነገር በጋራ ይወሰን የሚል ከሆነ በስሩ ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ ምን ሊደ
142 views06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 17:42:43 በፍርድ ቤት 'የራስ አነሳሽነት' የሚሰጥ ብይን/ትዕዛዝ/ውሳኔ እና የመሰማት መብት
#አብርሃም ዮሐንስ

በወንጀል ጉዳይ በተለይ ደሞ በፍትሐብሔር ክርክር ወቅት ፍርድ ቤት በራሱ አነሳሽነት ብይን/ትዕዛዝ/ውሳኔ የመስጠት ሰፊ ስልጣን አለው። ጥቂት ምሳሌ መጥቀስ ቢያስፈልግ አቤቱታ እንዲሻሻል: ተጨማሪ ማስረጃ እንዲቀርብ ትዕዛዝ መስጠት፤ የስረ-ነገር ስልጣኑ ላይ ብይን መስጠት እንዲሁም የመብት መቅረት በጊዜ ገደብ ሲወሰን በመብቱ አለመኖር ላይ ውሳኔ መስጠት /ለምሳሌ አሰሪው የሚከራከርበት የስንብት ምክንያት ድርጊቱ መፈፀሙን አሰሪው ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ ሲታሰብ አንድ ወር ካለፈው/ የአሰሪው የማሰናበት መብት ቀሪ ይሆናል። ይህ ከይርጋ የተለየ እንደመሆኑ በፍርድ ቤቱ በራሱ ሊነሳ ይችላል። ከጊዜ ገደብ ጋር በተያያዘ የሰ/መ/ቁ 17361 ቅፅ 10 ይመለከቷል/

የራስ አነሳሸነት ለፍርድ ቤቱ አስገዳጅ ነው ወይስ 'የእንደፈቀደ' /discretionary/ ስልጣን የሚለው ጥያቄ መሰረታዊና አከራካሪ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ሌላ ይበልጥ መሰረታዊ ጉዳይ ጥያቄ ሆኖ ሲነሳ አይታይም።

በራስ አነሳሽነት የሚሰጥ ብይን/ትዕዛዝ/ውሳኔ መሰረታዊና እና ህገ-መንግስታዊ ከሆነው የመሰማት መብት አንጻር አሉታዊ እንደምታው በሚገባ አልተፈተሸም።

በምሳሌነት የስረ-ነገር ስልጣንን እንመልከት።
በተግባር እንደሚታየው ብሎም በስነ-ስርዓት ህጉ እና በሰበር ትርጉም ጭምር ድጋፍ ያገኘው አቋም አንድ ፍርድ ቤት የሰረ-ስልጣን ከሌለው በተከራካሪ ወገኖች ባይነሳም በራሱ አነሳሽነት መዝገቡን መዝጋት ይኖርበታል።
ግን በራስ አነሳሽነት ሲባል ምን ማለት ነው? በራስ አነሳሽነት የሚያስገነዝበው ፍርድ ቤቱ ነጥቡን መጀመሪያ በክርክር ወቅት ማንሳት አለበት ማለት ነው። የሚያነሳው ደግሞ ለተከራካሪ ወገኖች ነው። በዚሁ መሰረት ተከራካሪ ወገኖች በተነሳው ነጥብ ላይ ያላቸውን የህግ ክርክር ብሎም ማስረጃ ማቅረብ ወይም ማሰማት አስፈላጊ ከሆነ ማስረጃቸውን ሊያሰሙ ይገባል። የመሰማት መብት በግራ ቀኙ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን ፍርድ የሚያነሳውንም ነጥብ ይጨምራል።

በራስ አነሳሽነት ማለት ተከራካሪ ወገኖች ሳያውቁትና ሳይሰሙ በድንገት እና በድብቅ የሚሰጥ ብይን/ትዕዛዝ/ውሳኔ ማለት አይደለም። ፍርድ ቤት የስረ-ነገር ስልጣኑን የሚወስነው በግምት ሳይሆን በተረጋገጡ አግባብነት ያላቸው ፍሬ ነገሮችና በህጉ ትርጓሜ ላይ በመመስረት ነው። በፍሬ ነገር /ማስረጃ/ እና የህግ ትርጉም በሚመለከት ጉዳይ ተከራካሪ ወገኖች የመሰማት መብት አላቸው።

ነገሩን እንደሚከተለው እንመልከተው።
የስረ-ነገር ስልጣን መቃወሚያ በተከራካሪ ከተነሳ ተቃራኒው ወገን የመሰማት መብት ካለው ፍርድ ቤት ስላነሳው ብቻ ይህን መብቱን የሚያጣበት አንዳችም የህግ መሰረት የለም።
በተጨማሪም ተካራካሪዎችን ያላሳተፈ 'የራስ አነሳሽነት' ለስህተት የመጋለጡ ዕድል በጣም ሰፊ ነው።

እንበልና በመኪና አደጋ የተነሳ ከውል ውጭ ሀላፊነት ክስ ሲቀርብ ተከሳሽ በመልሱ ላይ የጠቀሰው አድራሻ ተከራካሪዎች የተለያየ ክልል ነዋሪዎች መሆናቸውን ይጠቁማል። ሆኖም ተከሳሽ የጠቀሰው ቤተሰቡ የሚኖርበትን አድራሻ እንጂ መደበኛ የንግድ ስራውን የሚያከናውነውና አብዛኛውን ጊዜ የሚኖረው አደጋው በደረሰበት ክልል ነው። ተከሳሽ የስረ-ነገር ስልጣን አላነሳም። ከሳሽም በዚህ ነጥብ ላይ ማስተባበያ አላቀርበም። ካሁን አሁን ፍርድ ቤት በራሱ አነሳሽነት የስረ-ነገር ስልጣኑን በዚህ ላይ ተመስርቶ ብይን ሊሰጥ ይችላል በሚል ስሌት ማስተባበያ እንዲያቀርብም አይጠበቅበትም። ፍርድ ቤት በራሱ የሚያነሳቸው ነጥቦች በርካታ እንደመሆናቸው የትኛውም የህግ ባለሞያ ሁሉንም ከወዲሁ ሊያውቃቸው ሆነ ሊገምታቸው አይችልም።

ፍርድ ቤት በራስ አነሳሽነት የስረ-ነገር ስልጣኑን የመወሰን ሀሳብ ካለው ማድረግ ያለበት ተከራካሪ ወገኖች የተለያየ ክልል ነዋሪዎች መሆናቸውን እንደ ምክንያት ይዞ በራሱ ጊዜ መዝገቡ መዝጋት አይደለም። መጀመሪያ ከስልጣን ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤቱ የስረ-ነገር ስልጣኑን ለመወሰን የተከራካሪ ወገኖች አድራሻ መጣራት እንዳለበት ለተከራካሪ ወገኖች በመንገር በዚህ ረገድ የህግ ክርክር ካላቸው በተጨማሪም ክርከራቸውን የሚደግፍ ማስረጃ ካላቸው እንዲያቀርቡ ዕድል መስጠት አለበት። ይህ ሲሆን ነው ተከሳሽ የንግድ ስራውና አብዛኛውን ጊዜ የሚኖረው አደጋው በደረሰበት ክልል መሆኑን ከሳሽ ማስተባበያ ማቅረብ የሚችለው። በተጨማሪም አንድ ሰው የንግድ እና የቤተሰብ መኖሪያ ስፍራው የተለያየ ከሆነ ለስረ-ነገር ስልጣን አወሳሰን የየትኛው ክልል ነዋሪ ነው? የሚለው የህግ ጭብጥ ግራ ቀኙ ሊከራከሩበት ይገባል።

በአጠቃላይ 'በራስ አነሳሽነት' ማለት ፍርድ ቤት በራሱ ጊዜ የሚያነሳው ሆኖም ባነሳው ነጥብ ላይ ግራ ቀኙ የመሰማት መብታቸው ተጠብቆ ከተከራከሩ በኋላ የሚሰጥ ብይን/ትዕዛዝ/ውሳኔ ማለት እንጂ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ ሳያውቁት ፍሬ ነገሩን በራሱ ገምቶ፣ የህጉን ትርጉም ለብቻው አውጥቶ አውርዶ መጨረሻ ላይ ድንገት የሚሰጠው ብይን/ትዕዛዝ/ውሳኔ ማለት አይደለም።
137 views14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 18:44:22 #የአላባ ጥቅም ውል

የአላባ መብት ማለት የሚጠቀሙበትን ነገር ከመጠበቅ ግዴታ ጋር ከዚሁ ነገር ላይ በሚገኙት ነገሮች (ፍሬዎች) ወይም መብቶች ለመጠቀምና ለመገልገል የሚሰጥ መብት ነው፡፡

ይህም መብት የሚንቀሳቀሱና በማንቀሳቀሱ ንብረቶች መብቶች ወይም በአንድ ጠቅላላ ንብረት ላይ ሊሆን የሚችል ነው:: በማለት በፍትሐ ብሔር ህግ አንቀጽ 1309 (1) እና (2) ላይ ተቀምጧል፡፡

በመሆኑም ተገልጋዮች የአላባ ጥቅም ውልን ለመዋዋል ወደመስሪያ ቤታችን ሲመጡ ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡

. በህግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣

. ተዋዋይ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጫ ሰነድ፣

. የንብረት ባለቤትነት ማስረጃ፣

. በማንኛውም መልኩ ንብረቱ ከእዳና እገዳ ነጻ መሆኑን ማረጋገጥ፣

የአላባ ውሉ የሚደረገው በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ከሆነ የሁለት ምስክሮቻዉና የታደሰ መታወቂያ፣

. የአላባ ሰጪ እና ተቀባይ የታደሰ መታወቂያ፣

. የአላባ ሰጪው ያገባ ወይም ያላገባ ከሆነ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት /ውክልና፣

. የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ የንግድ ዋና ምዝገባ እና እንደአስፈላጊነቱ ቃለ-ጉባኤ፡፡
174 views15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 18:43:34 አንድ የመንግሥት ሠራተኛን በኃላፊ በተፃፈ ደብዳቤ ብቻ ከሥራ ማሰናበት ሕገ መንግሥታዊ ነውን?

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 37(1) መሰረት ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በሕግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት ሕገ መንግሥታዊ መብት ያለው ስለመሆኑ ተደንግጓል። በተጨማሪም በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 42 ስር ለሠራተኞች የተደነገጉ በርካታ መብቶች አሉ። በተለይም ከዚህ የሕገ መንግሥቱ ድንጋጌ አርዕስት መረዳት አንደሚቻለው ሠራተኞች በሕገ መንግሥቱ የተጠበቀላቸው የሥራ ዋስትና መብት ያላቸው መሆኑን መረዳት ይቻላል። በሕገ መንግሥቱ ለሠራተኞች የተጠበቀው የሥራ ዋስትና መብት ከሚከበርበት መንገድ ውስጥ አንዱ ሠራተኞች በሕግ አግባብ ከተቀመጠው ሂደት እና አሠራር ውጪ ከሥራቸው መባረር የሌለባቸው መሆኑ ነው። ሠራተኞች በሥራ ቦታ ለሚያጠፉት ጥፋት በሕግ አግባብ በተቀመጠው የዲስፕሊን ሂደት የመዳኘት መብት አላቸው። ይህ መብት ከላይ በተጠቀሰው የሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 37(1) መሰረት የሚተገበር ነው።
በዚህ ድንጋጌ መሰረት በተለይም የመንግሥት ሠራተኞች በዲስፕሊን ጥፋት ከሥራ የሚሰናበቱት ጉዳያቸውን ለማየት እና ፍርድ ወይም ውሳኔ ለመስጠት በሕግ ስልጣን ባለው አካል ብቻ ነው። በሕግ በግልፅ ከተደነገገው አግባብ ውጪ አንድ የመንግሥት ሠራተኛ ተገቢውን ክርክር ሳያደርግ፤ ያለውን ማስረጃ በማቅረብ እራሱን ሳይከላከል አንዲሁም ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ላለው አካል ይግባኝ አቅርቦ ሳይከራካር ከሥራ ሊሰናበት አይችልም።.......ይቀጥላል
131 views15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ