Get Mystery Box with random crypto!

የጅግጅጋ ከተማ ባይፓስ(Bypass) መንገድ ግንባታ በትኩረት እየተከናወነ ነው። ጅግጅጋ ፣ ነሐሴ | ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

የጅግጅጋ ከተማ ባይፓስ(Bypass) መንገድ ግንባታ በትኩረት እየተከናወነ ነው።

ጅግጅጋ ፣ ነሐሴ 23/2014 ዓ.ም. ፦ የከተማዋን የትራፊክ መጨናነቅ የሚያስቀረው የጅግጅጋ ባይፓስ (Bypass) መንገድ ግንባታ ሥራ እየተካሄደ ነው።
ሰባት (7) ኪ.ሜ የሚረዝመው የመንገድ ፕሮጀክቱ የፌደራል መንግስት በመደበው 672 ሚሊዮን ብር ወጪ ነው ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው።
'ባይፓስ' መንገድ አንድ ዋና ማሳለጫ ባላቸው ከተሞች በውጭ የሚገነባና ተሽከርካሪዎች ከተማ ውስጥ መግባት ሳያስፈልጋቸው አልፈው እንዲሄዱ የሚያገለግል ነው።
መንገዱ የከተማዋን የትራፊክ መጨናነቅና አደጋ ለመቅረፍ ታልሞ ነው የሚገነባው።
ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘው ይርጋለም ኮንስትራክሽን ሲሆን በእስካሁኑ የግንባታ ሂደት የአፈር ቆረጣና ሙሌት፣ የሰብቤዝ፣ የውኃ መፋሰሻ ቱቦ ቀበራና የ94 ሜትር ድልድይ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
አስፋልት ለማንጠፍ የሚረዱ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችም እየተሠሩ ነው።
የመንገድ ግንባታው ዋነኛ ግብዓት የሆነው የሲሚንቶ ዕጥረት ለስራው ፈተና እንደሆነበትም ታውቋል።
ችግሩን ለመቅረፍ የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ።
የማማከሩን ስራ እያከናወነ የሚገኘው ደግሞ ኤልዳ ኢንጅነሪንግ ኮንሰልታንትሲ ሲሆን የድጋፍና ክትትል ሥራውን እያከናወነ ይገኛል።
የመንገድ ግንባታው በትላልቅ ከተሞች የመንገድ ደረጃ በኮንክሪት አስፋልት እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን፥ የእግረኛ እና የብስክሌት መተላለፊያ እንዲሁም የአረንጓዴ ሥፍራ በፕሮጅክቱ ተካትተውበታል።
የጅግጅጋ ባይባስ ግንባታ ሲጠናቀቅ የንግድ እንቅስቃሴዎችን በማሳለጥ፤ ለከተማዋ ዕድገት ምቹ ዕድል ይፈጥራል።
በክልሉ ለሚደረጉ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችም የጎላ ሚና አለው። መንገዱ 30 ሜትር የጎን ስፋት አለው።