Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ለሰራተኞቹና አመራሮቹ የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየሰጠ ነው የኢትዮጵ | ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ለሰራተኞቹና አመራሮቹ የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየሰጠ ነው
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ሰራተኞች እና አመራሮች የአቅም ግንባታ ላይ ያተኮረ ሰልጠና ዛሬ በቢሾፍቱ ከተማ ተጀመረ።
ስለጠናው በአራት የተለያዩ ዘርፎች ላይ ያተኮረ ሲሆን እነሱም Project management፣ Project planning and implementation፣ Good governance in public sector administration እና 4.Human resource management ናቸው፡፡
ስልጠናው እየተሰጠ የሚገኘው አሀጉር አቀፈ እውቅና ባለው East and South Africa Training Management Institute (ESAMI) እና ሌሎች የስለጠና እና ምርምር ተቋማት በጣምራ ነው። በዘርፉ የረጅም አመታት ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች በመሰጠቱ ስለጠናው የበለጠ ውጤት ተኮር ይሆናል። የስለጠናው በቨርቿል እና በአካል እየተሰጠ ይገኛል። በዛሬ እለት በቢሾፍቱ ከተማ የተጀመረው ይህ ስልጠና ተቋሙ መንግስትና ህዝብ የጣለውን አገራዊ ሀላፊነት ይበልጥ በብቃት እንዲወጣ ይረዳዋል።
በስልጠናው ከ110 በላይ የተቋሙ ሰራተኞች እየተሳተፉ የሚገኙ ሲሆን የቀሰሙትን ዕውቀት ለሌሎችም በማካፈል ስራን ለማቀላጠፍ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ኢመአ በክረምት ወራት አቅዶ እያከናወናቸው ከሚገኘው በርካታ ስራዎች አንዱ የሰራተኞቹን አቅም በተለያዩ ስልጠናዎች በማዳበር በአዲሱ የስራ አመት ውጤታማ ስራ ማከናወን ነው። ስለጠናውም እንደየ ኮርሱ ይዘትና ስፉት ከአንድ እስከ ሶስት ሳምንት የሚቆይ ይሆናል።

በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et