Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር መላው ሰራተኞች እና አመራሮች ሁለተኛ ዙር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብ | ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር መላው ሰራተኞች እና አመራሮች ሁለተኛ ዙር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ዛሬ አከናወኑ ።
የዋናው መስሪያ ቤት፤ የአለም ገና ማሰልጠኛ ማዕከላት ሰራተኞች እና አመራሮች ናቸው በእንጦጦ ፖርክ አካባቢ 3ሺህ ችግኞችን ዛሬ በስፍራው የተከሉት ።
የበጀት አመቱን ሁለተኛ ዙር የችግኘ ተከላ መርሃ-ግብር ሁሉም በተቋሙ ስር የሚገኘው ምርምር ማዕከልን ጨምሮ ዲስትሪክቶች ፥ ሴክሽኖች እና ማሰልጠኛ ማዕከላትም ሶስት መቶ ሺህ ችግኞችን በዛሬው ዕለት በየአካባቢያቸው ተክለዋል ።
ኢመአ ባለፋት ዓመታት ሀገራዊ አረንጓዴ አሻራን በማሳረፍ ሀላፊነቱን ይበልጥ እየተወጣ ነው ።
በኢመአ የጊንጪ ማሰልጠኛ ጣቢያም የራሱን የችግኘ ማፍያ ፕሮጀክትን እውን በማድረግ ለአካባቢው ህብረተሰብ ፣ለተቋማት፣ የተለያዩ የችግኘ አይነቶችን በማበርከት ላይ ይገኛል።
የተቋሙ ሰራተኞችም አረንጓዴ አሻራን ማሰረፉ ያለው ጥቅም የጎላ በመሆኑና ሀገራዊ ባህል እየሆነ በመምጣቱ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።
የተከሉትን ችግኞች በቀጣይ መንከባከብ ላይ በትኩረት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል።
ባለፉት ዓመታት በኢመአ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ከ3ሚሊየን በላይ ሀገር በቀል ችግኞች ተተክለዋል።
ዘንድሮም አንድ ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ግብ የተያዘ ሲሆን ከወዲሁ በስኬት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ ነው
ኢመአ የችግኝ ተከላ-መርሃ ግብሩ ተገቢውን ሳይንሳዊ ሂደት ጠብቆ እንዲተከል፤
ከአካባቢው ስን- ምህዳር ጋር የሚጣጣሙ ሀገር በቀል ችግኞች እውን እንዲሆኑ፤
ከተተከሉም ብኋሏ የመጸደቅ ምጣኔው እንዲረጋገጥ፤ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ ነው።

በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ ethiopian roads authority
› ቴሌግራም @ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et