Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ 'የብሪክስ' አባል አገራትን ለመቀላቀል ጥያቄ አቀረበች የኢትዮጵያ መንግስት በፈረንጆቹ | ሪፖርተር (Ethiopian Reporter)

ኢትዮጵያ "የብሪክስ" አባል አገራትን ለመቀላቀል ጥያቄ አቀረበች

የኢትዮጵያ መንግስት በፈረንጆቹ 2009 የተመሰተረተውንና ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ በጥምረት የመሰረቱትን "ብሪክስ" (BRICS) የተሰኘ የአገራት ስብስብ ለመቀላቀል ጥያቄ ማቅረቧ ተገለጸ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ መለስ አለም (አምባሳደር) በሳምንታዊ መግለጫቸው እንደገለጹት ኢትዮጵያ የብዙ አለማቀፍ ተቋም መስራች መሆኗን ጠቅሰው የተባበሩት መንግስታት፣ የአፈሪካ ህብረት እና የገለልተኛ አገሮች ንቅናቄና መስራችና ጠንካራ ተሳትፎ ያላት አገር ናት ብለዋል፡፡

በመሆኑም አሁን እየተለወጠ ባለው የዓለም ሁኔታና የኃይል አሰላላፍ አንጻር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምን ለማረጋገጥ የሚረዱ ዓለም አቀፍ ተቋማት አባል በመሆን መንግሥት እንደሚሠራ ተናግረዋል። "ከእነዚህ ተቋማት መካከል አንዱ 'ብሪክስ' ነው ፣ ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል ጥያቄ ቀርቧል፣ በጎ ምላሻ ያገኛል ብለን እናስባለን ፣ ክትትልም የምናደርግበትም ይሆናል" ብለዋል ቃል ቀባዩ፡፡

የብሪክስ አገራት ላለፉት አስርት አመታት ለዓለም ኢኮኖሚ እድገት 50 በመቶ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ሲሆን ፣ ይህም ቡድኑን በዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ልማት ግንባር ቀደም ተጽዕኖ ፈጣሪ እያደረገው መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ለዓብነትም 17 በመቶ የሚሆነው ዓለም አቀፍ ንግድ በብሪክስ አገራት የተያዘ ሲሆን ፣ በአሁኑ ወቅት የአገራቱ ድምር የውጭ ምንዛሪ ክምችት 4 ትሪሊዮን ዶላር እንደሚሆን ይገመታል።
አንዳንድ ተንታኞች የብሪክስ አገራት ኢኮኖሚ እ.ኤ.አ. በ2027 የቡድን 7 (አሜሪካ ፣ ጃፓን፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ብሪታንያ፣ ካናዳ እና ጣሊያን) ያክል ትልቅ ሊሆን እንደሚችል ይተነብያሉ።
የብሪክስ አገሮች ከዓለም የቆዳ ስፋት 30 በመቶውን የሚሸፍኑ ሲሆን ፣ 45 በመቶ የሚሆነው የዓለም ህዝብ መኖሪያ እንደሆኑም መረጃዎች ያመለክታሉ።