Get Mystery Box with random crypto!

ብርቱካን ሚደቅሳ መልቀቂያ አቀረቡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በገዛ | ሪፖርተር (Ethiopian Reporter)

ብርቱካን ሚደቅሳ መልቀቂያ አቀረቡ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በገዛ ፈቀዳቸው ከኃላፊነት ለመልቀቅ በመወሰን መልቀቂያ ማቅረባቸውን አሳወቁ።

ብርቱካን ሚደቅሳ በኦፋሳላዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለጹት ከኃላፊነት ለመልቀቅ የወሰኑት በጤና ችግር ምክንያት ነው

"ጤናዬን በሚገባ ለመጠበቅ የረጅም ጊዜ እረፍት የሚያስፈልገኝ ሆኖ በመገኘቱ ከ ነሀሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቦርድ ሰብሳቢነቴ በገዛ ፍቃዴ መልቀቄን ለተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ጽህፈት ቤት ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም አሳውቄያለሁ" ብለዋል።

በሚቀራቸው ጊዜ ያልተጠናቀቁ ስራዎችን የማጠናቀቅ እና አስተዳደራዊ ሽግግር የመፈፀም ሃላፊነቶችን እንደሚወጡም አስታውቀዋል።