Get Mystery Box with random crypto!

ብርሃን ባንክ ለዋና መሥሪያቤቱ ህንጻ ያሸነፈውን ዲዛይን ይፋ አደረገ ብርሃን ባንክ ለዋና መሥሪያ | ሪፖርተር (Ethiopian Reporter)

ብርሃን ባንክ ለዋና መሥሪያቤቱ ህንጻ ያሸነፈውን ዲዛይን ይፋ አደረገ

ብርሃን ባንክ ለዋና መሥሪያቤቱ ህንፃ ግንባታ ዲዛይን ለማሠራት ባወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ አሸናፊ ሆኖ የተመሰጠውን ዲዛይን ይፋ አደረገ።

ባንኩ ባወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ ላይ 16 ኩባንያዎች የተሳተፉ ሲሆን ተሳታፊዎቹ ካቀረቧቸው ዲዛይኖች መካከል አሸናፊ የሆነው ዲዛይን ግንቦት 2 ቀን 2015 ዓ.ም. ምሽት በተካሄደ ፕሮግራም ላይ ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሠረት ባንኩ በሰንጋ ተራ አካባቢ በተረከበው 5400 ካሬ ሜትር መሬት ላይ ለሚያስገነባው ህንፃ MAE ኮንሰልቲንግ ኤንድ ኢንጂነርስ በተባለው ድርጅት የቀረበው ዲዛይን አሸናፊ ሆኖ ተመርጧል። በተመረጠው ዲዛይን መሠረት የሚገነባው የባንኩ ዋና መሥሪያቤት ህንፃ ከ 51 በላይ ወለሎች እንደሚኖሩት ታውቋል።

በዴጃው ኮንሰልቲንግ የተሰራው የህንፃ ዲዛይን ሁለተኛ ደረጃ አሸናፊ ሲሆን ፣ በአዲስ መብራቱ ኮንሰልቲንግ ኤንድ ኢንጂነርስ የቀረበው ዲዛይን ደግሞ ሦስተኛ ወጥቷል።