Get Mystery Box with random crypto!

ይህም ቃሌ ይመዝገብልኝ…!! • በስልክ ለምታነቡ ረጅም ጽሑፍ ነው። ገተት የመሰለ ጽሑፍ። ረጅም | ዘመድኩን በቀለ

ይህም ቃሌ ይመዝገብልኝ…!!

• በስልክ ለምታነቡ ረጅም ጽሑፍ ነው። ገተት የመሰለ ጽሑፍ። ረጅም ጽሑፍ ማንበብ የማትወዱ አጭሬዎች ይለፋችሁ። ቆይቼ የኮመንት መስጫ ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ። መልካም ንባብ።

"…ኢትዮጵያ ትነሣለች። ኢትዮጵያ ታሸንፋለች። ኢትዮጵያ በላይዋ ላይ ተጣብቀው የመዘመዟት፣ ሲመዘምዟት የኖሩት፣ ሊመዘምዟት ቋምጠው ያሰፈሰፉት የውስጥም፣ የውጪም ጠላቶቿ እንደጢስ በነው፣ እንደጉም ተነው አይናችን እያየ፣ ጆሮአችን እየሰማ ብን ብለው ይጠፋሉ። ዳውን ዳውን ኢትዮጵያ እያሉ በአውሮጳ፣ በካናዳና በአሜሪካ ጎዳናዎች ላይ የፈከሩ የትግሬና የኦሮሞ የዳያስጶራ ቃጥራ ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎችም የት እንደደረሱ ሳናውቅ ብን ብለው ይጠፋሉ። የማናውቀው ከዚያ በፊት ሰምተነውም፣ አይተነውም የማናውቀው ዐቢይ አሕመድ የተባለ የኢትዮጵያውያን አራጅ፣ አሳራጅ፣ ደማቸውን ለአውሬው ገባሪ ድንገት ብቅ እንዳለው ለኢትዮጵያ መድኅን የሚሆናትም ድንገት ይከሰታል። ይሄ ይመዝገብልኝ። 

"…በኢትዮጵያ ምድር ላይ ከአንዲቷ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በቀር በኢትዮጵያ ምድር ላይ አረመኔዋ የሰይጣን ውላጇ፣ ሥጋ ለበሷ ሰይጣን አጋንንቷ ህወሓት አሰፍታ የበተነችው፣ ያደለቻቸው የኦሮሞው የግብፅ ባንዲራ፣ የእርሷም የቬትናም ባንዲራ እና የሌሎችም ሁሉ ጥብቆ ግማታም፣ ክርፋታም ሸታታ የሽንት ጨርቅ በሙሉ ይወገዳል። ይቃጠላል። ይጠፋል። በኢትዮጵያ ምድር ከነፃዋ ምድር ከኢትዮጵያ ሰንደቅ ውጪ ሌላ ኮተት መያዝ፣ ማውለብለብ ያስገድላል፣ ከፍ ያለ ቅጣትም ያስከትላል። በኢትዮጵያ ምድር ከኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ውጩ ወደ ውጪ የሚባልበት ጊዜም ሩቅ አይሆንም።

"…የዐማራ ምድር ጀምሮታል። የህወሓትን የሽንት ጨርቅ ከብአዴን ቢሮ በቀር ካስወገደው ቆይቷል። ትግሬዋ ህወሓት ይዛው ከቆየችው ወልቃይት ምድር ላይ እንኳ የወያኔም፣ የብአዴንም የሽንት ጨርቅ ዳይፐራቸው ወርዶ የሰይጣኗ የህወሓት ዓርማም ተነሥቶ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ፣ ሰይጣናዊው የዲያብሎስ ምልክት የሌለበት፣ ባለአምባሻው፣ ባለ ኮከቡ ባንዲራ ተወግዶ ያ የበረከት፣ የፍቅር፣ የመስዋዕትነት ሰንደቅ ዓላማችን ተተክቷል። ወልቃይትም የፍቅር ሃገር ሆናለች። በጀት ሳይመደብላት በራስ አቅም ልማቷን ታጣድፈው ይዛለች።

"…አሁን ህወሓት እየከሰመች ነው። ትከስማለችም። ለሥልጣኗ ስትል የትግራይን ወጣት ጭዳ ያደረገችው ህወሓት በጊዜ ሂደት ትከስማለች። እሷ ስትከስም፣ ስትሟሽሽ፣ ስትበን፣ ስትተን ደግሞ ኢትዮጵያ ቀን ይወጣላታል። የብርሃን ጮራም ይፈነጥቅላታል። ጋንግሪኗ ህወሓት ስትቆረጥ የኢትዮጵያም፣ የትግራይም የዐማራና የኦሮሞ፣ የአፋርና የሱማሌም ህዝብ እርፍ ይላል። የኢትዮጵያ ትንሣኤም ይቀርባል። የትግሬና የዐማራ ህዝብ፣ የጽዮንና የግሸን ማርያም ልጆች፣ የአፄ ቴዎድሮስ፣ የአፄ ዮሐንስ፣ የአፄ ምኒልክና የንጉስ ሚካኤል ልጆችም ይታረቃሉ። ከዚያ የሚሆነውን አብሮ ማየት ነው። ህወሓትና ብአዴን ከተወገዱ፣ ትግሬና ዐማራ ታቦተ ጽዮንና ግሸን ከመስቀሉ ስር፣ በነጋሺ መስጊድም ተሰብስበው ከመከሩ ለላው ዕዳው ገብስ ነው። ሌላው በጣም ቀላል ነው። በትግሬና በዐማራ እልቂት ጮቤ እየረገጠ ያለው፣ በኦርቶዶክሳውያኑ መመናመን፣ መጨፋጨፍ፣ በሰሜኖቹ በነጃሺ ልጆች መተራረድ ከበሮ እየደለቀ እየጨፈረ ያለው አካል በተራው ዋጋውን ያገኛል። አሁን እንደ ጀማሪ ብረት አንሺ ጎረምሳ ያዩትን ሁሉ ቁጫጭ፣ ጉንዳን አድርገው የሚመለከቱ ሁሉ ቀኑ ሲደርስ ያኔ ማየት ነው።

"…በህወሓት ጦስ ትግሬ በትግራይም፣ ከትግራይ ውጪም ፍዳውን እያየ ነው። ዐማራም እንደዚያው። ሁለቱም ከዐማራ ክልልም ሆነ ከትግራይ ክልል ወደ አዲስ አበባ መግባት ተከልክለዋል። በኦሮሞ ስም የሚነግደው የህወሓት ጥፍጥፉ ኦህዴድኦነግ በአዲስ አበባ ፍተሻ በሚያደርግበት ወቅት እንኳ መታወቂያ ላይ ስሙ የዐማራ ወይም የትግሬ የሆነ ሰው ፍዳውን ነው የሚያየው። እሬቻውን ነው የሚያበላውም። ይወገራል፣ ይታሰራል፣ እንደከብት ወደ ዘብጥያ ይወርዳል። ይናቃል። ይተፋበታል። በምልጃ በጉቦ ይፈታል። ዐማራውን ፋኖ ነህ፣ ትግሬውን ወያኔ ነህ በማለት እያጠፋው ነው ይሄ ሰይጣናዊ መንግሥት። እናም ይሄን አጋንት ለማስወገድ መፍትሄው ዐማራው ብአዴንን፣ ትግሬው ህወሓትን፣ ኦሮሞው ኦህዴድኦነግን አስወግዶ በአንድነት መጋፈጥ ነው። ኦሮሞው እንኳ አሁን በሁለት ምክንያት ኦህዴድኦነግን መጋፈጥ ላይችል ይችል ይሆናል። አንደኛው ተረኛ ነኝ፣ ተጠቃሚ ነኝ በሚለው ኦሮሞ ሲሆን ሁለተኛው ኦነግንናኦህዴድን ማሸነፍ አልችልም ብሎ ራሱን አኮስምኖ የተቀመጠው ኦሮሞ ነው። ዐማራ፣ ትግሬና ኦሮሞ ህዝብ ለህዝብ ከመከሩ ግን እነዚህ አጋንንቶች ግማሽ ቀን አይፈጁም ነበር።

"…ዐብይ አሕመድ በአሜሪካኑ፣ በምዕራባውያኑ ሥልጣኑን ለማጽናት ሲል ጴንጤ የሚመስል ነገር ግን በውስጡ እልም ያለ የዓረብ ተላላኪ የወሓቢያ እስላም ነው። ደምበኛ አባ ገዳ ነው። ጨፍጫፊ፣ ዘር አጥፊ አውዳሚ ነው። ትግሬና ዐማራ ህዝብ ለህዝብ መመካከር ጀምሮ በቶሎ በፕሮቴስታንቱና በአክራሪ የወሀቢያ እስላም የተደቀነበትን መንግሥት መር ጭፍጨፋ ካላስቆመ የቃልኪዳን ህዝብ ስለሆነ ቢተርፍ እንጂ ገና ይቀጠቀጣል። ገና ይረሸናል። ኦሮሞ እያበበ፣ ዐማራና ትግሬ ለማኝ የሆናል። ዐመዳም ስደተኛ ይሆናል። ሃገር ሠርቶ ሃገር አልባ ይሆናል። አለቀ።

"… እኔ መስሚያዬ ጥጥ ስለሆነ፣ የብልጽግና አጋንንታዊ የጴንጤም ሆነ የወሓቢያ ሰራዊት ሰደበኝ አልሰደበኝ ደንታ ስለማይሰጠኝ መራር እውነቱን እፅፈዋለሁ። ቢያንስ ለታሪክ ይቀመጣል። ፕሮፌሰሩ፣ ዶክተሩ፣ ምሑራኑ እንደኔ ደፍረው ባይናገሩም፣ እኔ ደንቆሮው፣ እኔ የሀረርጌው መራታ፣ እኔ መቶ ኪሎ ድልብ መሃይሙ ዘመዴ ግን እጽፈዋለሁ። ትግሬ ህወሓትን፣ ዐማራ ብአዴንን ለቅመህ ካላጸዳህ ትጠፋለህ፣ ትሰደዳልህ፣ ትንከራተታለህ፣ ትወድማለህ። ትሞታለህ። ዋይዋይ በዐማርኛ፣ ወይአነ ወይአነ በትግርኛ ሙሾ ስታወርድ ትኖራለህ። ይመዝገብልኝ።

"…ትናንት ማታ በመለስ ዜናዊ እንኩትኩቱ ወጥቶ የነበረውን የወያኔ ጄነራል የታደሰ ወረደን ቃለመጠይቅ ሥራዬ ብዬ ስሰማው ነበር። ትንፋሹ እየተቆራረጠ፣ ከንፈሩ እየደረቀ፣ ምራቅ እያጠረው እምጫ እምጫ እያደረገ ሲናገር እየሰማሁት ነበር። በሚጠላው አማርኛ ሲዘበዝብ ነበር። በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ጊዜ ለምን ከባረንቱ እንመለሳለን? በማለቱ በመለስ ዜናዊ ተጎድቶ ልምሾም ሆኖ የነበረው ጀነራል ታደሰ ወረደ ሲናገር ያሳዝን ነበር። እኔ በእሱ ውስጥ ወያኔ ሞታ ትግሬ ድኖ ነው ያየሁት። ወያኔ ስትሞት ትግሬ ይድናል። የትግሬ በሽታው ህወሓት ናት። ብአዴን ሲሞት ዐማራው ይድናል የዐማራው በሽታ ብአዴን ነው። ኦህዴድኦነግ ሲሞት ኦሮሞው ይድናል የኦሮሞ በሽታው ኦህዴድኦነግ ነው። ኦፌኮን እርሱት እሱ ምች ነው። በዳማከሴ ይጠፋል።

"…እናም የወያኔው ጄነራል እያማጠ፣ እ አ እ እያለ ሲናዘዝ አየሁት። ደስስስም አለኝ። ታዴ ምንአለ አትሉኝም። ትግራይ ሃገር እንኳ ብትሆን ጎረቤቷ ዐማራ ነው። ይሄን መቀየር አንችልም። ትግራይ ሃገር ብትሆን የኤርትራ ህዝብ ጎረቤት ነው። ይሄን መቀየር አንችልም። የዐማራ ህዝብ ወንድም ህዝብ ነው። ብላብላ ብሎ ብዙ ከዘበዘበ በኋላ "የህወሓት ሰራዊት ከዐማራ ልዩ ኃይልና፣ ከዐማራ ፋኖ ጋር እንዳይዋጉ መታዘዙን፣  ተዋግተው ቢማረኩ እንኳ የዐማራ ልዩ ኃይልና የዐማራ ፋኖ ወዲያውኑ በፍጥነት እንዲለቀቁ እየተደረገ እንደሆነ ሲናገር ሰምቼው ደነቀኝ።  ነገርየው ፖለቲካ እንደሆነ፣ ቢጨንቀው እንደሆነ ቢገባኝም የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አሠራር ግን