Get Mystery Box with random crypto!

ማነው የሚያድነኝ (ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ ቁ-፪) ለዚህ ለኃጢአት ከተሰጠ ከህይወት መርገምን | ኦርቶዶክሳዊ ወጣት

ማነው የሚያድነኝ
(ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ ቁ-፪)

ለዚህ ለኃጢአት ከተሰጠ
ከህይወት መርገምን ከመረጠ
ለሞት ከተሰጠ ከንቱ ኑሮ
ማነው የሚያድነው ሞትን ሰብሮ
           
ሥጋ በሥጋ ህግ ይስበኛል
መንፈስ በመንፈስ ጥግ ይጠራኛል
ለየትኛው ጌታ ተገዝቼ
የቱን እመርጣለሁ አንዱን ትቼ
ኃጢአት እሰራና ይጨንቀኛል
አምላኬ ሲለየኝ ይሰማኛል
ጌታዬ ሲለየኝ ይሰማኛል
አምላኬ ሲለየኝ ይሰማኛል
          
በኃጢአት ለመኖር በዚህ ዓለም
የአምላክን ትእዛዝ በማጣመም
በስርቆት በዝሙት በስካር
በዲያቢሎስ ፈቃድ ስንኖር
የኋላ የኋላ ውርደት ነው
አምላክ በክንዶቹ ያልያዘው
የጨለማ ጉዞ ምኑ ይጥማል
ዐይን እያሳወረ ያዋርዳል
           
መላእክት ከሰማይ ያለቅሳሉ
የእግዚአብሔር ቅዱሳን ያነባሉ
በኃጢአት ተማርከን ስንወሰድ
ሰይጣን ድል አግኝቶ ስንዋረድ