Get Mystery Box with random crypto!

ስለ ቼክ ይርጋ ጊዜ ።።።።።። ።።።።።።። ቼክ የወጣበት ቀን ከግምት ሳይገባ በቼክ | የህግ ተማሪዎች ህብረት🇪🇹

ስለ ቼክ ይርጋ ጊዜ
።።።።።። ።።።።።።።
ቼክ የወጣበት ቀን ከግምት ሳይገባ በቼክ ላይ ከተፃፈው ቀን አንስቶ በሚከተሉት 6 (ስድስት) ወራት ውስጥ እንዲከፈል ባንክ መቅረብ እንዳለበት በንግድ ሕግ ቁጥር 855 ሥር ተመልክቷል፡፡

በንግድ ሕግ ቁጥር ቁጥር 881(1) ሥር ደግሞ በቼክ የሚገደዱ ሰዎች ላይ ቼኩን የተቀበለው ሰው ክስ ማቅረብ የሚችለው ቼኩን ለክፍያ ባንክ ለማቅረብ የተወሰነው ጊዜ ካለፈ ጀምሮ እስከ (6) ስድስት ወር ድረስ ነው፡፡
በመሆኑም ቼክ የተቀበለ ሰው፣ ቼክ ሰጪው ላይ የፍትሀ-ብሄር ክስ ማቅረብ የሚችለው ቼኩ ላይ ከተፃፈው ቀን አንስቶ በ 1 (አንድ) ዓመት ጊዜ ውስጥ ነው፡፡