Get Mystery Box with random crypto!

#Daily_Tips Economic Crisis እና Financial Crisis ማለት ምን ማለት ነው? | Ethiopian Business Daily

#Daily_Tips
Economic Crisis እና Financial Crisis ማለት ምን ማለት ነው?

የአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ትከክለኛውን መስመር ተከትሎ መሄድ ሲያቅተው እና ወደ አለመረጋጋት ደረጃ ሲደርስ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተከስቷል ይባላል፡፡

በአንድ ሀገር ውስጥ ትክክለኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መኖሩን ከምናረጋግጥባቸው መንገዶች መካከል ዋነኞቹ፡- ዝቅተኛ የስራ አጥነት ደረጃ (ከ 4 ከመቶ ያልበለጠ) ሲኖር፤ የተረጋጋ እና ዝቅተኛ የሆነ የዋጋ ንረት ደረጃ (ከ 4 ከመቶ ያልበለጠ) ሲሆን፤ በተመሳሳይ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ መውረድ (Deflation) ሁኔታ ያለመኖር፤ ምክንያታዊ የጠቅላላ ሀገራዊ የምርት መጠን (GDP) እድገት ሲኖር፤ የውጪ ንግድ ሚዛን ሲያድግ፤ ከፍተኛ የሆነ የምርታማነት ደረጃ ሲኖር፤ ማለት ሲሆን፡ በተቃራኒው የአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ መለኪያዎች (Indicators) ከላይ ከተጠቀሱት ደረጃዎች ለየት ያለ ሲሆን ኢኮኖሚያዊ ቀውስ (Depression ወይም Recession ብለው የሚጠሩትም አሉ) ተፈጥሯል ይባላል፡፡

ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ሃብትን በአግባቡ ካለመጠቀም፤ ደካማ ከሆነ የፋይናንስ ተቋማት አሰራር፤ ደካማ የሆነ የኢኮኖሚ ፖሊሲ አተገባበር ሲኖር፤ ወዘተ ከሚመነጭ ምክንያት ሊፈጠር ይችላል፡፡ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተፈጠረ ማለት አጠቃላይ ኢኮኖሚው፤ ህዝቡ እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት ሊዳከሙ ይችላሉ፡፡ #ለምሳሌ፡- ስራ አጥነት እና የዋጋ ንረት ሲጨምር የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ በቀጥታ እንደሚጎዳው ግልጽ ነው፡፡
.
.
.
Read More
https://telegra.ph/Daily-Tips-Economic-Crisis--Financial-Crisis-06-04

@Ethiopianbusinessdaily