Get Mystery Box with random crypto!

የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በማደያዎች የነዳጅ ግብይትን በዲጂታል የማካሄድ የሙከራ ትግበራ | Ethiopian Business Daily

የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በማደያዎች የነዳጅ ግብይትን በዲጂታል የማካሄድ የሙከራ ትግበራ  ሥራ መጀመሩን አሳውቋል።

ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ደግሞ በመላ ሀገሪቱ የዲጂታል የነዳጅ ግብይት ይጀመራል ተብሏል።

ዛሬ በአዲስ አበባ ለሙከራ የተጀመረው የዲጂታል ግብይት በሁሉም ተሽከርካሪዎች እና በሁሉም ማደያዎች ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

ግብይቱ በዲጂታል መሆኑ ምርት እንዳይባክን እና የተሳለጠ ግብይት እንዲኖር እንደሚያደርግ ነው ሚኒስቴሩ የገለፀው።

የነዳጅ ግብይቱ በ #ቴሌብር አማራጭ የሚከናወን ነው የተባለ ሲሆን በዚህ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ሁሉም የመንግስት እና የግል ተሽከርካሪዎች ቁጥጥር ይደረግባቸዋል ተብሏል።

ሚኒስቴሩ በቅርቡ የትራንስፖርት ትኬት በዲጂታል እንደሚጀመር አሳውቋል።

Via - ኤፍቢሲ | ቲክቫህ
@Ethiopianbusinessdaily