Get Mystery Box with random crypto!

ውቅያኖስ ጠላቂው ሮቦት በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተሰራው ኦሽን ዋን ኬ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሰ | Ethiopian Artificial Intelligence Institute

ውቅያኖስ ጠላቂው ሮቦት

በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተሰራው ኦሽን ዋን ኬ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሰው መሰል ሮቦት የሰጠሙ የመርከብ ፍርስራሽ እና ሌሎች አካላትን ለማሰስ ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡

ሮቦቱ አምስት መቶ ሜትር ድረስ በመጥለቅ በውሃ አካላቱ ግርጌ ላይ የሚገኙ በሰዎች ተደራሽ ለመሆን እጅግ አዳጋች የሆኑ የሰጠሙ ቁሶችን ሁኔታ ለመቃኘት እያገለገለ ነው፡፡

የሮቦቱ የዕይታ አድማስ በ3ዲ የተዋቀረ እና ባለሙሉ ቀለም ምስሎችን ያላንዳች ችግር ማስተላለፍ የሚችል ስለመሆኑም ሲ.ኤን.ኤን አስነብቧል፡፡

በውሃ አካላቱ ወለል ላይ ሆነው ሮቦቱን የሚቆጣጠሩ ሰዎች ሮቦቱ የሚነካውን እያንዳንዱን ቁስ እና የውሀውን ግፊት ሳይቀር እራሳቸው ውሃ ውስጥ ያሉ እስኪመስላቸው ድረስ በሮቦቱ መቆጣጠሪያ ሥርዓት አማካኝነት እንደሚደርሳቸው ተመላክቷል፡፡

ከመስከረም ጀምሮ በነበረው የሮቦቱ ቆይታ በተለያየ ጊዜ የሰጠሙ መርከቦች እና አውሮፕላኖችን ለመቃኘት እንዳገለገለ ተገልጿል፡፡

ኦሽን ዋን ኬ ለሰው ልጆች እጅግ አደገኛ የሆኑ ጥልቅ የውሃ ውስጥ ፍለጋዎች በሮቦቶች የሚከወኑበትን አዲስ መንገድ እንድናይ የሚረዳ የመጪው ጊዜ ተስፋ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡