Get Mystery Box with random crypto!

የዓለም ጤና ድርጅት I-DAIR ከተባለ የቴክኖሎጂ ተቋም ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡ ድርጅ | Ethiopian Artificial Intelligence Institute

የዓለም ጤና ድርጅት I-DAIR ከተባለ የቴክኖሎጂ ተቋም ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

ድርጅቱ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ዲጂታል የጤና ሥርዓቶች ዙሪያ የሚደረጉ ምርምሮችን አስመልክቶ International Digital Health and AI Research Collaborative (I-DAIR) ከተባለ ተቋም ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት አድርጓል፡፡

ትብብሩ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ዲጂታል የጤና ሥርዓቶች ዙሪያ የሚደረጉ ዓለም አቀፍ ምርምሮች አካታች፣ ኃላፊነት የሚሰማቸው እና ውጤታማ እንዲሆኑ የማስቻል ዓላማን የሰነቀ ነው፡፡

በስምምነቱ መሠረት ሁለቱ ተቋማት የዲጂታል አብዮት አበርክቶዎችን በመጠቀም አጣዳፊ የሆኑ የጤና ተግዳሮቶችን ለመፍታት እንደሚሰሩ ተመላክቷል፡፡

በዚህም ዲጂታል የጤና ሥርዓቶች እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን አስመልክቶ በሚደረጉ ምርምሮች፣ በማበልፀግ ሂደቶች እና ዘርፉን ማስተዳደርን በተመለከቱ ጉዳዮች የዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ሀገራት ተሳትፎ አፅንኦት እንደሚሰጥበት ተገልጿል፡፡

በሂደቱም በእነዚህ ሀገራት ለሚገኙ ወጣት ተመራማሪዎች እና ሥራ ፈጣሪዎች ልዩ ትኩረት እንደሚደረግ የዓለም ጤና ድርጅት ይፋ ያደረገው መረጃ ያመላክታል፡፡

I-DAIR መቀመጫውን ስዊዘርላንድ በማድረግ በዓለም ዙሪያ የሚስተዋሉ የግለሰብ እና የሕብረተሰብ የጤና ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ በዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ላይ በሚደረጉ የትብብር የምርምር እና ልማት ሥራዎች ላይ የሚሰራ ተቋም ነው፡፡