Get Mystery Box with random crypto!

የዘንድሮው የ10ኛ ክፍል(የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና) አይሰጥም! 10ኛ ክፍል ይሰጥ የነበረው | Ethiopian Students

የዘንድሮው የ10ኛ ክፍል(የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና) አይሰጥም!

10ኛ ክፍል ይሰጥ የነበረው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከዚህ ዓመት (2012 ዓ/ም) ጀምሮ አይሰጥም። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማረጋገጥ እንደቻለው የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከወዲሁ ቅድም ዝግጅት ጀምሯል። በአዲሱ የትምህርት እና ስልጠና ፍኖተ ካርታ መሰረት ቀደም ብሎ በ10ኛ ክፍል ይሰጥ የነበረው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከ2012 ዓ/ም ጀምሮ በ12ኛ ክፍል እንዲሰጥ ምክረ ሃሳብ መቅረቡ ይታወቃል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጣይ ሳምንታት ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ያደርሳችኃል።

@tikvahethiopia @tsegabwolde