Get Mystery Box with random crypto!

ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የአለባበስ ሕግ ይፋ ሊደረግ ነው! የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የ | Ethiopian Students

ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የአለባበስ ሕግ ይፋ ሊደረግ ነው!

የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የአለባበስ ስነምግባር ደንብን ለመወሰን በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሚኒስቴር የተጠናው ጥናት ተጠናቆ ከጥር 2012 ጀምሮ ይፋ ሊደረግ ነው።

ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መደበኛ ተብሎ በጥናት የሚረጋገጠውን አለባበስ፣ ሀይማኖታዊ አለባበስ እና ባህላዊ አለባበሶችን ይደነግጋል የተባለው ይህ መመሪያ እስከዛሬ በየዩኒቨርሲቲው ተበታትኖ የሚገኘውን የተማሪዎች መተዳደሪያ ደንብ ይተካል ሲልም ሚኒስቴሩ ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል።

‹‹በርካታ ተማሪዎች ሥነ ምግባር የጎደለው አለባበስ በመጠቀም መማር ማስተማሩን ሲያውኩ ነበር›› በማት ለአዲስ ማለዳ የገለፁት የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር #ደቻሳ_ግሩም ‹‹በተለይም ፀጉራቸውን አንጨባረው የሚመጡ በርካታ ወንድ ተማሪዎች በየዩኒቨርስቲው ማየት የተለመደ ነው›› ሲሉም ገልፀዋል።

በአዲሱ መመሪያ መሰረትም የፓርቲ አርማ ያለበት ልብስ እና ለግጭት የሚዳርጉ የተለያዩ አለባበሶችን ለብሰው የሚመጡ ተማሪዎችን የሚገድብ እና ችግሩንም የሚፈታ እንደሆነ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ
https://telegra.ph/ETH-10-07


Via አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia