Get Mystery Box with random crypto!

EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_orthodox_tewahdo_books — EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_orthodox_tewahdo_books — EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopian_orthodox_tewahdo_books
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.90K
የሰርጥ መግለጫ

ቅዱሳት መጻሕፍትን እንለዋወጥበት ዘንድ እንዲሁም አዳዲስ የሚወጡ መንፈሳዊ መጻሕፍትን እንድንተዋወቅበት ተከፈተ

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-02 17:28:18
5.5K views14:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-02 17:28:17
4.8K views14:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-30 19:26:28
4.6K views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 20:41:34

4.9K views17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-19 07:11:50
4.7K views04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-28 15:06:55 Dawit Kebede
የብርሃን እናት !
ባልተለመደ መልኩ በዕንባ ብዕር የተጻፈን የብርሃን እናት የተሰኘ መጽሐፍ በልብ ሥቃይ አንብቤ ከተፈወስኩ በኋላ በተለመደ መልኩ በገጽ ብዛቱ ፣ በምዕራፉ እና በሥነ ጹሐፍ ውበቱ መጀመር የበሽተኛ ሐኪም ፣ የወንጀለኛ ዳኛ ፣ ቀበጥ ቁስለኛ ስላደረገኝ ዐይኑ የበራለት ኹሉን ትቶ ማየት በመቻሉ የተሰማውን ደስታ ለመግለጽ እንደሚቸኩል ኹሉ "መቼም ልብን አኮማትሮ ደስ ይበልህ ማለት የለምና " የልቤን ደስታ ብቻ ለመግለጽ ቸኮልኩ !
ሄሮድስ ጌታን ብቻ ያሳደደ መስሎት እናቱን ጭምር ስደተኛ አድርጎ ነበር ። ዛሬም እናቱን ብቻ ያሳደዱ መስሏቸው ጌታንም ጭምር ከእስራኤል ልባቸው ላሳደዱ ኹሉ ይህ የብርሃን እናት መጽሐፍ ዳግማዊው ሄሮድስን ከልባቸው ገድሎ "የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ዳግማዊ ሄሮድሶች ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል ልብህ ተመለስ" የሚያሰኝ ይመስለኛል ።
አዳምና ሔዋን ሆይ ከዚህ ቀደም ያለመታዝ ቁስላችሁን አመጣጥ አጥብቆ መርማሪ ባለመኖሩ ለአንዳዶቻችን እስካሁንም መድኃኒት ያልተገኛችሁ በሽተኞች ፤ ለሌሎቻችን መድኃኒት ያላስፈልጋችሁ ጤነኞች ለብዙዎቻችን ደግሞ ብቸኛ በሽተኞች ነበራችሁ ዛሬ ግን የእናንተንም የኛንም በሽታ ከነመድኃኒቱ አጥብቆ መርማሪ የብርሃን እናት አግኝታችኋልና ደስ ይበላችሁ !
የብርሃን እናትን የሚያነብ ኹሉ ቅዱስ ባስልዮስ ሐኪም እነደመሆኑ ስለ ሰው ልጅ የመጀመሪያ ያለመታዘዝ በሽታ ሲተነትን ፤ ቅዱስ ኤፍሬም እና ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ ደግሞ ከበሽታው ይልቅ ስለ መድኃኒቱ ሲራቀቁ ያገኛቸዋል ። ከኹሉ ይልቅ እኔን የደነቀኝ ግን የበሽታውም የመድኃኒቱም ጠቢብ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ጉዳይ ነው ! ይህ አባት የብርሃን እናት ታማኝ ምስክሯ ነውና በዚህ መጽሐፍም ትውልድ ኹሉ ከእርሱ ጋር እንዲተዋወቅ የብርሃን እናት ለወዳጇ ሄኖክ አደራ ያለችው ይመስለኛል !
አንዳንድ ጊዜ ትጉህ ፣ የበሽታ መንስኤን ጠንቅቆ አዋቂ እና መርማሪ ባለ መድኃኒት ሲገኝ ከዚህ ቀደም ለአንድ በሽታ ብቻ ሲውል የነበረ መድኃኒት የሌላ ዘመን አመጣሽ ደዌ አስተማማኝ መፍትሔ ሆኖ እንደሚገኝ ኸሉ በብርሃን እናት ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ከዚህ በፊት ከምናውቃቸው የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ መድኃኒት ጥቅሶች ውስጥ ከዚህ ቀደም ለመድኃኒትነት ያልዋሉ እና ለአንድ በሽታ ብቻ ሲውሉ የነበሩትን መድኃኒቶች ለአያሌ የዘመናችን በሽታዎች መፍትሔ እንዲሆኑ ያደረገ ብልህ ባለመድኃኒት መሆኑን የምትረዱት መጽሐፍን እንደኔ ስታነቡ ብቻ ነው !
ሌላው ያስደነቀኝ ነገር ጸሐፊው ለሚያነሳቸው ሃሳቦች በሙሉ ነቢያቱም ፣ ሃዋርያቱም ፣ ቅዱሳኑም ተሽቀዳድመው "እኔ ምስክር ልሁንህ ! እኔ ምስክር ልሁንህ !" ብለው የተረባረቡበት መንገድ ነው ። ይህን ላስተዋለ ዲያቆን ሄኖክ "እናንተ ብቻ የቅዱሳን ወዳጅ ኹኑ እንጂ ያለ ምስክር ብቻችሁን ላለመቅረታችሁ የብርሃን እናት ኀያው ምስክሬ ናት ! " እያለን ይመስለኛል !
ጌታ መድኃኛችን የሆነው ሕማሙ ምስክር ለሆነው ለቅዱስ ዮሐንስ በምድር ላይ የቀረች አንዲት ሀብቱን እናቱን ከመስቀሉ ሥር እንደሰጠው ይታወቃል። ቢሰጥ የማያልቅበት ነውና ዛሬም በየዘመናቱ የሕማሙ ምስክር ለሆኑትም እናቱን እንካችሁ ብሎ ይሰጣቸዋል። ሕማማት በተሰኘው መጽሐፉ ልባችንን ወደ ቀራኒዮ ለወሰደው የቁስሉ ምስክር ሄኖክም " እናትህ እነኋት" ብሎት የብርሃን እናትን ወደ ቤቱ ወሰዳት.....መልካም ንባብ
ዲ/ን ዶ/ር ዳዊት ከበደ
የካቲት 18 2014 ዓ.ም
5.6K views12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-26 06:36:14
4.5K views03:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-25 20:18:30
አዲስ መጽሐፍ
4.4K views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-24 21:38:47 በአማን ነጸረ
ተኀሥሦ ከ‹‹ዓርብ ጨዋታ››ዎች ከፍ ትላለች፡፡ Advanced and standardized የዓርብ ጨዋታ ልትባል ትችላለች፡፡ (ራሴን ለመነስነስ ይፈቀድልኝና) ከፍ ካደረግናት በውስጧ የሚነሡት አሳቦች ጥናት እንኳ ባይሆኑ በየራሳቸው የጥናት ቢጋር (research proposal) መሆን ይቻላቸዋል፡፡ በቅኝቷ፡- አንድ በዚህ ዘመን ያለ ኦርቶዶክሳዊ አንባቢ ወጣት የአገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሃይማኖታውያን መጻሕፍትን በሚያነብበት ጊዜ ወደ ሕሊናው ብልጭ ከሚሉበት አሳቦች የጐሉትን ታስሳለች፡፡ ‹‹ዘመናውያን›› የጥናትና የምርምር ሰዎች ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ለጥያቄና ለተኀሥሦ ዝግ እንደሆነችና እምነትና ሥርዓቷ ያለምንም ተዋሥኦ አንድም በነገሥታት፣ አንድም በጳጳሳት የተጫነባት እንደሆነና ከዚህ የወጣን ሁሉ በጭፍን እንደምታወግዝ ተደርጎ መቅረቡ ጉርብጥብጥ ይላታል፡፡ ሲጐረብጣት በኢትዮጵያ የተካሄዱ ጉባኤያትን ከነገጽታቸውና የተነሡ ልዩ ልዩ ብሔራውያን የነገረ ሃይማኖትና ሥርዓታት ጥያቄዎችን በይዘት ከፋፍላ ከይዘቷ ግማሹን ለዚህ ጉዳይ ሰጥታ ትፈታትሻለች፡፡ ከውጭ ብቻ ሳይሆን ከውስጥም ቢሆን ተፈትና ያላለፈች ቤተ ክርስቲያን የለችንም ለማለት ነዋ! እንደገና የምዕራቡን ተፅዕኖ ለመቋቋም የምሥራቃውያን አበው መጻሕፍት እጅጉን አጋዦች መሆናቸውን በሙሉ ልብ ብትቀበልም በምሥራቃውያኑ ፍትፍት ውስጥ እንደ ምርቅ ሆነው በነገረ ክርስቶስ ከሚመጡት የባሕርይ፣ የፈቃድና የግብር የምንታዌ አስተምህሮዎች ውስጥ ቤተ ክርስቲያናችን የምታስተምረው የግብርና የፈቃድ ተዋሕዶ ቸል የተባለ መስሎ ሲሰማት ትንደቀደቃለች፤ የምሥራቃውያን የሱታፌ አምላክ ሐተታ በነገረ ክርስቶስ ከሚሰብኩት የምንታዌ አስተምህሮ ተደባልቆ በመነገሩ ትቆጣለች፡፡ ለባሕርይና ለግብር ምንታዌ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌን እንደ ምስክር አድርጎ ‹‹የኢኦተቤክ እንዲህ ታምናለች!›› ማለትን ስትሰማ ይነዳትና የሊቁን ብሂል ኬልቄዶናዊ ቀለም መንቀስ ያምራታል፡፡ ተኀሥሦ፡- በሃይማኖት ከማይመስሉን ወገኖች ስለተተረጐሙ መጻሕፍት፣ በሃይማኖት ከማይመስሉን ወገኖች መካከል ተገኝተው ሳለ በቅድስና ስለተጠሩ ሊቃውንትና ገዳማውያን፣ ምሥራቃውያን በኑፋቄ የሚጠሯቸው ሳያንስ በቤታችን አንዳንድ ምንጮች በሚገርም መልኩ በኑፋቄ ስለተጠሩ ሁለት ታላላቅ ቅዱሳን አበውና በእነርሱ ዙሪያ ስላለው ልዩ ልዩ አመለካከት የሊቃውንትንና የነገረ መለኮት ምሁራንን ምላሽ ለመስማት የሚጓጓ ምልከታ አላት፡፡ ይህቺን ንዑስ ርእስ (‹‹በነፋቄ የተጠሩ ቅዱሳን›› የምትለውን) እንደ ተኀሥሦ ግኝት ለማየት ይዳዳኛል፡፡
--
ተሐድሶ የሚለው ቃል በብዙ ምሥጢር በቤተ ክርስቲያናችን የሚነገር ቃል ሆኖ ሳለ በቈናጽል እጅ ገብቶ አሉታዊ ገጽታ በመላበሱ ትብከነከናለች፤ ተብከንክናም አትቀር ቃሉን በቃለ መጻሕፍት በየአንጻሩ በምኅፃር ለማንጠር ትፍጨረጨራለች፡፡ ተኀሥሦ ለተሐድሶ ቀና አመለካከት የላትም፤ የቀረውን እምባዝም አትነቊር አትነቅፍ (በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚቃጣው የተሐድሶ ቅሠጣ ሃይማኖታዊ ዝማዌ ነው የሚል የፀና እምነት አላት)፡፡ ለሌላው አንባቢ ሞጋች (argumentative) ሳይሆን ገላጭ (descriptive) አቀራረብ ስላላት ትጐረብጥ አይመስለኝም፡፡ ተኀሥሦ ‹‹ወንእመን እንበለ ተኀሥሦ - ሳንመራመር እንመን›› የሚለውን የተከበረና ለምሥጢራት የሚነገር ቃል ወዲህ አውደልዳዩ ወዲህም ምናቡን እምነትና ታሪክ ለማድረግ የሚቃጣው እንደገና ወዲህ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሰዎችን ነጻ ፈቃድ (ግእዛን) እንደማታከብር ይልቁንስ ሕሊናትን ግዑዝ፣ ድንዙዝ፣ ዕዙዝ አድርጋ እንደምተቀርጽ የሚሰብኩ የሚናገሩ ድምፆች ስትሰማ ትታወካለች፡፡ ተኀሥሦዋን ቀጥላ በምሥጢረ ሥላሴ የሚነገረውን ውስጣዊና ውጫዊ ግብር እያሰላሰለች ወዲህ የቆጋ ዘመዶቻችንን ወዲህም ፕሮቴስታንታውያን ዘመዶቻችንን እነ ጳውሎስ ፈቃደን ጐነጥ ታደርጋለች፡፡ ሥራዎቻቸውን በክብር አንብባ የሚደነቀውን አድንቃ ስታበቃ ቅሬታዋን ኧረ ምነ! ምነ! ውስጣዊና ውጫዊ ግብር (Economic and Immanent Trinity) ባታደበላልቁብነ! ስትል ትማረራለች፡፡ ተኀሥሦ እንዲህ ናት፡፡ አሁን ተኀሥሦ አማረ አበበ ( #ብራና መጻሕፍት) ሹሞ ሸልሞ በቀጣይ ሳምንት በአደባባይ ሊገልጣት እየኳላት እያሸሞነሞናት ነው፡፡ ባገኛችሁበት ያዙልኝ!
4.2K views18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-24 21:37:42
አዲስ መጽሐፍ
3.5K views18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ