ተስፋ ቆርጠን ነበር በሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ተስፋ ቆርጠን ነበር ኤማሁስ የሄድነው፣ በግፍ ስለሞተ ይቤዠናል ያልነው፣ ስልሳውን ምእራፍ በሀዘን ተራመድን፣ የሚያቃጥል ፍቅሩን/ሞቱን እያሰብን/።(፪) በመንገዳችን ላይ አንድ እንግዳ መጥቶ፣ ጠየቀን በብርቱ መሃላችን ገብቶ፣ ዓለም የሰማውን ባያውቀው ደነቀን፣ እውነቱን ገለጽነው በእምነት ተናገርን። አዝ= = = = = በስራና በቃል ብርቱ ነብይ ነበር፣ በአይሁድ ተገድሎ አደረ መቃብር፣ ይህ ሁሉ ከሆነ ሶስተኛ ቀን ሆነው፣ በምኩራባችን ላይ መምህሩን ካጣነው። አዝ= = = = = ዛሬ በማለዳ አዲስ ነገር ሰማን፣ በመቃብር የለም ተነስታል ጌታችን፣ ሴቶች አስገረሙን ስጋው የለም ሲሉ፣ መላእክቱም ታዩ ህያው ነው እያሉ። አዝ= = = = = መጻህፍትን ገልጾ በሚነግረን ነገር፣ ልባችን በሚስጢር ይቀልጥብን ነበር፣ አይናችን ተይዞ እኛ መች አወቅነው፣ ቀኑ መሽታል እና በቤት እደር አልነው። አዝ= = = = = እንጀራውን ቆርሶ በእጃችን ሲሰጠን፣ ባይናችን ላይ ያለው አዚሙ ለቀቀን፣ እንዳላዋቂ ሰው ከኛ ጋራ ያለው፣ የትንሳኤው ጌታ ለካስ ኢየሱስ ነው።(፫) @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox 2.1K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 08:35