Get Mystery Box with random crypto!

'ጉድለት የሌለብሽ ምስጋናን የተሞላሽ እመቤቴ ማርያም ሆይ በክብር በጸጋ ከመንፈሳውያን ከመላእክት | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ጉድለት የሌለብሽ ምስጋናን የተሞላሽ እመቤቴ ማርያም ሆይ በክብር በጸጋ ከመንፈሳውያን ከመላእክት ነገድ፣ ሥጋን ከለበሰ ከሰው ሁሉ አንቺ ትበልጫለሽ። በማኅበር መካከል የተመሰገንሽ ነሽ። በተሰበሰቡት ፊት ትወደሻለሽ። ክብርሽን የሚመስላት ሌላ ክብር የለም። ሥርዓቷ ሌላ ነው፤ ሕጓም የተለየ ነው። እመቤቴ ሆይ የሰላም ምንጭ መገኛዋ፣ የትንቢት ልምላሜ መውረጃዋም አንቺ ነሽ። ለርኅራኄ ውኃ መገኛ የይቅርታ ምንጪ ጉድጓድም አንቺ ነሽ። ፍቅርሽን እየተከተልሁ አልለቃትም። መከራ፣ የጥፋት ዘመንም ሲመጣ የበደልን፣ የኃጢአትን ሰንሰለት ከእኔ አስወግጂ። ጸሎቴም በፍቅርሽ ገመድ ተነጥቃ በፊትሽ ትድረስ። ዘወትርም በፊትሽ ትገለጥ፡ ለዘለዓለሙ አሜን።"
      -እንዚራ ስብሐት ዘቅዳሜ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox