Get Mystery Box with random crypto!

ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት አርብ ቅድስት ቤተክርስቲያን/ነፍሳት/ ይባላል በዚህ ዕለት | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት
አርብ
ቅድስት ቤተክርስቲያን/ነፍሳት/
ይባላል
በዚህ ዕለት ቅድስት ቤተክርስቲያን ተብሎ የተሰየመበት ምክንያት በጥቂቱ በቤተክርስቲያን ዙሪያ ሰባት ነገሮችን እንድናስብ ነው፡፡ እነዚህም፡-
፩. ቅድስት ቤተክርስቲያን በሞቱ እና በትንሣኤው መመስረቷን እናስባለን፡፡
፪. አምላካችን ራሱን አሳልፎ እንደሰጣት እናስባለን፡፡
፫. እርሱ ራሷ እርሷ ደግሞ አካሉ እንደሆነች እናስባለን፡፡
፬. ቅድስት ቤተክርስቲያን መሰረቷ የነብያት እና የሐዋርያት ቃል መሆኑን እናስባለን፡፡
፭. በደሙ ስለመታጠቧ እናስባለን።
፮. ከነገድ ከቋንቋ ሁሉ ስለመመረጧ እናስባለን፡፡
፯. ለዘላለም እንዳትናወጽ በእርሱ ላይ ስለመታነጽዋ እናስባለን፡፡ (ሥርዓተ አምልኮ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ገጽ፻፰፯)

ነፍሳት ከሲዖል የወጡበት ጌታችን በዕለተ ዓርብ በመልዕልተ መስቀል ቅዱስ ሥጋውን ቆርሶ ክቡር ደሙን አፍስሶ በአካለ ነፍስ ወደ ሲዖል ወርዶ በሲዖል ያላችሁ ውጡ በጨለማ ያላችሁ ተገለጡ ብሎ ግእዛነ ነፍስን ( የነፍስን ነፃነት ) ሰበከላቸው ሰይጣንን አሰረው ሲዖልን መዘበረው ነፍሳትን ነፃ አወጣቸው ልምላሜ ገነትን አወረሳቸው ይህ ዕለት በቀጣዩ በትንሣኤ ሳምንት ዓርብ እንዲታሰብ ነፍሳት የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል ፡፡

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox