Get Mystery Box with random crypto!

ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት ሐሙስ አዳም ይባላል ይህ ዕለት አዳም ሐሙስ (አዳም) የተ | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት
ሐሙስ
አዳም
ይባላል
ይህ ዕለት አዳም ሐሙስ (አዳም) የተባለበት ምክንያት አምላካችን እግዚአብሔር ለአዳም "ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" ብሎ ቃል የገባበት ዕለት በመሆኑ ይህንን ስያሜ አግኝቷል፡፡(ዘፍ፫፡ ፲፭) ፤ (መጽሐፈ ቀለሜንጦስ አንቀጽ ፰ እና መጽሐፈ አክሲማሮስ ዘዓርብ ቁ. ፲፫) ቤተክርስቲያን በዋናነት ለአዳም የተሰጠውን የተስፋ ቃል አምላካችን መፈጸሙንና የሰው ልጆች ሁሉ በትንሣኤው ከሞት ነጻ እንደወጡ በዚህ ዕለት ታስተምራለች፡፡
በዚህ ዕለት በአባታችን በአዳም በእናታችን በሔዋን አንጻር:-
፩. ከውድቀታችን ይልቅ መነሳታችንን
፪. ከባርነታችን ይልቅ ነጻነታችንን
፫. ከለቅሶአችን ይልቅ መጽናናታችንን
፬. ከሀዘናችን ይልቅ ደስታችንን
፭. ከመሰበራችን ይልቅ መጠገናችንን
፮. ከመታመማችን ይልቅ መፈወሳችንን
፯. ከድካማችን ይልቅ ኃይላችንን
፰. ከመረሳታችን ይልቅ መታወሳችንን
፱. ከጨለማችን ይልቅ ብርሃናነችንን
፲. ከፍርሃታችን ይልቅ ድፍረታችንን
፲፩. ከክህደታችን ይልቅ እምነታችንን
፲፪. ከጥላቻችን ይልቅ ፍቅራችንን
፲፫. ከመታወካችን ይልቅ ሠላማችንን
፲፬. ከሞታችን ይልቅ ሕይወታችንን
፲፭. ከመቃብራችን ይልቅ ትንሣኤአችንን የምናስብበት ዕለት ነው፡፡
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox