Get Mystery Box with random crypto!

በአባቶች ልመና በአባቶች ልመና እስኪ ልለምንሽ ፤ እኔማ ግብር የለኝ ለመቆም ከፊትሽ ፤ ረሃብሽ | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በአባቶች ልመና

በአባቶች ልመና እስኪ ልለምንሽ ፤
እኔማ ግብር የለኝ ለመቆም ከፊትሽ ፤
ረሃብሽን አሳስቢ ድንግል ሆይ እባክሽ።
አዝ-------------//
ግብሬን አውቀዋለሁ ምንም ምን ጽድቅ የለኝ /2/፤
ውኃ ያልጎበኘው አዳፋ ልብስ ነኝ።
አዝ----ጥምሽን
ለብሼ ሲያምርብኝ ጻድቅ እመስላለሁ /2፤
ድንግል ሆይ ታውቂያለሽ ውስጤን ጎስቁያለሁ።
አዝ----ልቅሶሽን
በኃጢያቴ ሳለቅስ ከጠዋት እስከ ማታ /2/፤
ድንግል ሆይ አትርሺኝ ሁኝልኝ አለኝታ።
አዝ-----ስደትሽን
ካጠጣሽው ውሻ ያን ጊዜ ተጠምቶ /2/፤
እኔም በምግባሬ አልሻልም ከቶ።
አዝ----ሃዘንሽን አሳስቢ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox