Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙር 116 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ እግዚአብሔር የልመናዬን ድምፅ ሰምቶአልና ወደድሁት። ² ጆሮውን | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መዝሙር 116
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እግዚአብሔር የልመናዬን ድምፅ ሰምቶአልና ወደድሁት።
² ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሎአልና በዘመኔ ሁሉ እጠራዋለሁ።
³ የሞት ጣር ያዘኝ፥ የሲኦልም ሕማም አገኘኝ፤ ጭንቀትንና መከራን አገኘሁ።
⁴ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራሁ፦ አቤቱ፥ ነፍሴን አድናት።
⁵ እግዚአብሔር መሓሪና ጻድቅ ነው፥ አምላካችንም ይቅር ባይ ነው።
⁶ እግዚአብሔር ሕፃናትን ይጠብቃል፤ ተቸገርሁ እርሱም አዳነኝ።
⁷ ነፍሴ ሆይ፥ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፥ እግዚአብሔር መልካም አድርጎልሻልና፤
⁸ ነፍሴን ከሞት፥ ዓይኔንም ከእንባ፥ እግሬንም ከመሰናከል አድኖአልና።
⁹ በሕያዋን አገር በእግዚአብሔር ፊት እሄዳለሁ።
¹⁰ አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ፤ እኔም እጅግ ተቸገርሁ።
¹¹ እኔም ከድንጋጤዬ የተነሣ፦ ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው አልሁ።
¹² ስላደረገልኝ ሁሉ ለእግዚአብሔር ምንን እመልሳለሁ?
¹³ የመድኃኒትን ጽዋ እቀበላለሁ፥ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።
¹⁴ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ።
¹⁵ የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።
¹⁶ አቤቱ፥ እኔ ባሪያህ ነኝ፥ ባሪያህ ነኝ፥ የሴት ባሪያህም ልጅ ነኝ፤ ሰንሰለቴን ሰበርህ።
¹⁷ ለአንተ የምስጋና መሥዋዕትን እሠዋለሁ፥ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።
¹⁸ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ፥
¹⁹ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ፥ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ በመካከልሽም። ሃሌ ሉያ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox