Get Mystery Box with random crypto!

ምስጋና..... እኛ የኢትዮጲያ ቡና እንስት ደጋፊዎች ክለባችን በ 2015 ዓ.ም የሚያደርጋቸውን | ቡናችን👆

ምስጋና.....

እኛ የኢትዮጲያ ቡና እንስት ደጋፊዎች ክለባችን በ 2015 ዓ.ም የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች ስፖንሰር እንዲደረጉ ማቅረቡን ተከትሎ አንድ ጨዋታ በኢትዮጲያ ቡና ሴት ደጋፊዎች ስም ለመግዛት እና የአዲስ አመት በአል የበጎ አድራጎት ስራዎችን ለመስራት እንቅስቃሴ የጀመርን ሲሆን የዚሁ አንድ አካል የሆነውን #አበባዮሽ በትላንትናው እለት ጨፍረን #130000 አሳክተናል።

1, ስታዲየም ዙሪያ ጤና ቡድን 10,000
2, አብዱልከሪም ናስር 10,000
3, ንጉስ 10,000
4, ዳጊ ኮፊ 15,000
5, ይስሃቅ ሽፈራው 5,000
6, ብዙአየሁ ዩሃንስ 10,000
7, ያያ ዘልደታ 5,000
8, ዳንኤል ረጋሳ 15,000
9, መኩሪያ 13,000
10, ኤልቢ 5,000
11, ክፍሌ ወልዴ 3,000
12, ብሬ B2 Burgers 2,000
13, ፌኔት ባር እና ሬስቶራንት 10,000
14, የሹ ታወር እና የኢትዮጲያ ቡና ደጋፊዎች 7,000
15, ሰኢድ (አምባሳደር ሞል) 5,000 ( ቃል የተገባ)
16, አረፋይኔ ሃውስ 5,000
17, ከሀ እስከ ፐ 10,000

.....በመጣንበት ሁሉ በሙሉ ልባችሁ ፈቅዳችሁ እና ደስተኛ ሆናችሁ የለገሳችሁን ውድ የኢትዮጲያ ቡና ቤተሰቦች ልባዊ ምስጋናችን ይድረሳችሁ በወጣ ይተካ

ይሄን እንድናሳካ ከጀርባ ሆናችሁ ያገዛችሁን እና ከኛ ጋር ከጠዋት ጀምሮ ጊዜያችሁን ገንዘባችሁን አውጥታችሁ አብራችሁ የዋላችሁ ወንድሞቻችን ብሩክ እስጢፋኖስ ሳሞራ ፣ ደሱ ከማንአንሼ ፣ ፍቄ የቡናውያን ዘር ሃረግ ፣አዲስ አለማየሁ ፣ወንደሰን ፀጋዬ ልባዊ ምስጋናችን ይድረሳችሁ።

አንድ ጨዋታ 250,000 ብር ነውና የጎደለንን አይታችሁ ህልማችን እውን እንዲሆን የምትሹ የኢትዮጲያ ቡና ቤተሰቦች አላማችንን እንድናሳካ ከጎናችን እንደምትቆሙ ልበ ሙሉ ሆነን እንናገራለን

ሁለተኛውን ጨዋታ እኛ እንስቶች እንደምንገዛው % እርግጠኛ ሆነን
እንናገራለን!! እናደርገዋለን ካልን እናደርገዋለን

መልካም በዓል ለሁላችን ይሁን
የቡናውያን ዘር ሀረግ

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc