Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ቦርድ ፕሬዝዳንት እና የክለባችን ስራ አስኪያጅ ከቡድኑ ጋር ውይይት | ቡናችን👆

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ቦርድ ፕሬዝዳንት እና የክለባችን ስራ አስኪያጅ ከቡድኑ ጋር ውይይት አድርገዋል።

የመ/አለቃ ፈቃደ ማሞ የኢትዮጵያ ቡና ከአመሰራረቱ አሁን እስካለበት ያሉት ሁነቶች ለተጫዋቾቹ አስረድተዋል።

" ...የመጣችሁት የባለ ብዙ ደጋፊ ባለቤት ወደሆነው ወደ ታላቁ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ነው። ይህ ደጋፊ በቀጣዩ የውድድር ዓመት ከእናንተ ብዙ ይጠብቃል።... ዘንድሮ ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ በዕድሜም ሆነ በስነ-ምግባር ጥሩ የሚባል የቡድን ግንባታ አከናውነናል። እናንተ በሜዳ ላይ የተቻላችሁን አድርጉ እኛም ከጎናችሁ ነን..." ብለዋል

አቶ ገዛኸኝም በአጠቃላይ በቡድኑ ዙሪያ ሐሳባቸውን ሰጥተው "... በ2015 ዓ.ም የውድድር ዓመት ክለቡም ሆነ ደጋፊው ከእናንተ ዋንጫ... ዋንጫ እና ዋንጫ ይጠብቃል። በመሆኑም ሙሉ ትኩረታችሁን ውድድሩ ላይ እንድታደርጉ እያሳሰብኩ ፤ ክለቡም ማንኛውንም ነገር አቅም በፈቀ መጠን አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ያደርጋል።..." ብለዋል።

ከነሐሴ 2/2014 ዓ.ም ጀምሮ በሴንትራል ሐዋሳ መቀመጫውን አድርጎ የቅድመ-ውድድር ዝግጅቱን ሲያደርግ የነበረው ክለባችን እስከ ጳግሜ 4/2014 ዓ.ም በሐዋሳ ያለውን ቆይታ አጠናቆ ቡድኑን ለበዓል የሚለቅ ይሆናል።

መስከረም 4/2015 ዓ.ም በድጋሚ በመሰባሰብ መቀመጫቸውን በክለባችን የተጫዋቾች ካንፕ በማድረግ ሊጉ እስኪጀመር ዝግጅት ያደርጋሉ።

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc