Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዲጂታል አማራጮቹ በተጨማሪ ደንበኞቹ ባሉበት ሁሉ አዳዲስ የቲኬት ሽያጭ | Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዲጂታል አማራጮቹ በተጨማሪ ደንበኞቹ ባሉበት ሁሉ አዳዲስ የቲኬት ሽያጭ ቢሮዎችን በመክፈት ላይ ይገኛል። አሁንም በሲ.ኤም.ሲ አካባቢ ፀሀይ ሪል እስቴት ፊት ለፊት በሚገኘው አዲስ-አፍሪካ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል የመጀመሪያ ወለል ላይ አዲስ የቲኬት ሽያጭ ቢሮ መክፈቱን ሲያበስር በታላቅ ደስታ ነው። ቀልጣፋ የትኬት ሽያጭ አገልግሎታችንን አቅራቢያዎ በሚገኙ ዘመናዊ የሽያጭ ቢሮዎቻችን ማግኘት ይችላሉ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ