Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ዛምቢያ በረራ ማድረግ የጀመረበትን 25ኛ ዓመት በሉሳካ በደማቅ ሁኔታ | Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ዛምቢያ በረራ ማድረግ የጀመረበትን 25ኛ ዓመት በሉሳካ በደማቅ ሁኔታ አከበረ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ዛምቢያ የሚያደርጋቸው በረራዎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን በማሳለጥ ረገድ ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙ አስምረውበታል።
አየር መንገዳችን አሁን ላይ ወደ ሉሳካ 11 እንዲሁም ወደንዶላ በሳምንት 5 ጊዜ በመብረር ላይ ሲገኝ፤ በቅርቡም ወደ ንዶላ የሚደረገውን በረራ ወደ 7 ከፍ በማድረግ ወደ ዛምቢያ የሚደረጉትን አጠቃላይ ሳምንታዊ በረራዎች 18 የሚያደርስ ይሆናል።