Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምንግዜም ለመንገደኞቹ ምቹ እና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት ብሎም የአቪዬ | Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምንግዜም ለመንገደኞቹ ምቹ እና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት ብሎም የአቪዬሽን ኢንደስትሪው የደረሰበትን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ስራ ላይ ለማዋል ባለው ቁርጠኝነት የቦይንግ አዲስ ምርት የሆኑትን በቅርብ ግዜ እና በሂደት የሚረከባቸውን የ20 ቦይንግ 777-9 አውሮፕላኖችን ለማስገባት የሚያስችለውን ስምምነት ዛሬ ከቦይንግ ጋር ተፈራርሟል። የB777-9 አውሮፕላን የቦዪንግ ስሪት የሆኑትን የB777 እና B787 አውሮፕላኖች ቴክኖሎጂዎችን ቀምሮ የያዘ የቦዪንግ ኩባንያ የቅርብ ጊዜ ምርት ነው። እንደከዚህ ቀደም ሁሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህንን አዲስ እና ግዙፍ አውሮፕላን በማዘዝ በአፍሪካ ቀዳሚው ሆኗል። ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የቦዪንግ ኩባንያ ለአስርት-ዓመታት የገነቡትን የንግድ ስምምነት የሚያጠናክር ነው።