Get Mystery Box with random crypto!

Liverpool Lfc sport ሊቨርፑል ኢትዮጵያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopialivepool — Liverpool Lfc sport ሊቨርፑል ኢትዮጵያ L
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopialivepool — Liverpool Lfc sport ሊቨርፑል ኢትዮጵያ
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopialivepool
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.25K
የሰርጥ መግለጫ

Liverpool Lfc sport ሊቨርፑል ኢትዮጵያ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-11 13:16:04
የሊቨርፑል ባስ ወደ ሆቴል ሲገባ በባንኮክ የሚገኙ የሊቨርፑል ደጋፊዎች አቀባበል ሲያረጉላቸው

@ethiopialivepool
1.5K viewsBoby Thiago, 10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 13:16:04
ሳላህ ስብስቡን ተቀላቅሏል

@ethiopialivepool
1.4K viewsBoby Thiago, 10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 13:16:04
ቀዮቹ የታይላንድ ዋና ከተማ ባንኮክ ገብተዋል።

በባንኮክ ያሉ የሊቬ ደጋፊዎች ኮከቦቹን በመውጣት ተቀብለዋቸዋል።

@ethiopialivepool
1.3K viewsBoby Thiago, 10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 07:51:41
ሞ በተጠናቀቀው ሲዝን ከማን ዪናይትድ ጋር

2 ጊዜ ገጠማቸው
5 ጎል አገባ
2 አሲስት አደረገ

አንዳንዶች ለማክሰኞው ጨዋታ ባልደረሰ እያሉ ነው እሱ እነሱ ላይ የማያገባው ካልተሰለፈ ብቻ ነው...

ዲያዝ ባለፈው ሲዝን ከዩናይትድ ጋር

1 ጨዋታ
1 ጎል
1 አሲስት

ጆታ ባለፈው ሲዝን ከዩናይትድ ጋር

2 ጨዋታ
2 አሲስት
1 ጎል

@ethiopialivepool
1.5K viewsBoby Thiago, 04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 07:49:40
ዳርዊን ኑኔዝ ፣ ቨርጂል ቫንዳይክ ፣ ቲያጎ አልካንትራ ፣ ናቢ ኬይታ ፣ ዲዮጎ ጆታ ፣ ኢብራሂማ ኮናቴ ፣ አሌክሳንደር አርኖልድ ፣ ኩርቲስ ጆንስ እና አንዲ ሮበርትሰን ወደ ባንኮክ ከሚያቀናው ቡድን ጋር አብረው
ተጉዘዋል። ነገርግን ሳላህ ፣ ፋቢንሆ እና አሌሰን ፕሌን ውስጥ ሲገቡ አልታዩም።

@ethiopialivepool
1.4K viewsBoby Thiago, 04:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 07:48:28
ለመጨረሻ ጊዜ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር በተገናኝንበት የወዳጅነት ጨዋታ 4-1 ነበር ያሸነፍነው የማሸነፊያ ጎሎቹን ማኔ ፣ ስተሪጅ ፣ ኦጆ እና ሻኪሪ ከመረብ አሳርፈዋል የማንችስተር ዩናይትድን የማስተዛዘኛ ጎል ደግሞ ፔሬራ አስቆጥሯል።

@ethiopialivepool
1.3K viewsBoby Thiago, 04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 07:45:01 #የቀጠለ.. ክሎፕ ስለ ኑኔዝ ፣ ራምሴ እና ካርቫልሆ

ክሎፕ በዳርዊን ኑኔዝ ላይ፦

"ከፊታችን ሲጫወት በጣም አስደናቂ ነበር። ቤንፊካን ለመግጠም ስትዘጋጅ የተጨዋቾችን ብቃት ጠንቅቀህ ታውቃለህ እኛ ስለ ተጋጣሚዎቻችን በሙሉ ሁሉንም ነገር እናውቃለን ስለዚህ ስለ ዳርዊን ጥራት በትክክል እናውቃለን በመጀመርያው ጨዋታ ከኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ስለተመለሰ ይጫወት አይጫወት እንደሆነ ግልፅ አልነበረም። እሱ በጨዋታው በጣም ጥሩ እንደነበረ ግልጽ ነበር  ነገር ግን ያኔ በቀጥታ ሲያዩት በጣም አስደናቂ ነበር ፣ 'ሃይሉ' እና ከቴክኒክ ጋር ያለው ውህደት ፣ ፍላጎት ፣ ብልህ እንቅስቃሴዎች ፣ እሱ ባደረሰብን ችግሮች ፣ ሁላችንም በእነዚህ ሁለት ጨዋታዎች በፍቅር ወድቀናል። በጣም ኃይለኛ ደቡብ አሜሪካዊ ተጨዋች ጥሩ ነገር ነው እሱን በማየታችን በእውነት በጣም አስደሳች ነበር እና እሱን ለማስፈረም ጥሩ እድል እንዳለን ስንገነዘብ ሁላችንም ተገኝተን ነበር እናም አሁን እሱን እዚህ በማግኘታችን ደስ ብሎናል''


ክሎፕ ስለ ካልቪን ራምሴ ጉዳት፦

“እንደ አለመታደል ሆኖ ካልቪን አሁን ከእኛ ጋር ልምምድ እየሰራ አይደለም ቀላል ጉዳት ነው ያስተናገደው? ማንም አያውቅም የሕክምና ምርመራውን ሲያደርግ አገኝተነዋል እስከ ዛሬ ድረስ ምንም ችግር የለበትም ነገር ግን ተጨዋቾችን ካልተንከባከብን የሕክምና ክፍሉ ለወደፊቱ ችግር እንዳለ ይነግረናል።
እሱን በዚህ ወጣትነት እድሜው ረጅም መንገድ ይጠብቀዋል በእነዚህ ጊዜያት በጣም ሀላፊነት አለብን ጉዳቱ ያንያህል ረጅም ጊዜ አይወስድም ግን ከቡድኑ ጋር እስከአሁን እየሰለጠነ አደለም ነገርግን ብዙ የአካል ብቃት ስራዎችን እየሰራ ነው። ስለዚህ እኔ እንደማስበው ጉዳቱ ብዙ ጊዜ አይፈጅም በስልጠና ላይ እስካሁን አላየሁትም ነገር ግን ስለ እሱ የተመለከትነው ነገር ሁሉ ስለ እሱ ሰምተናል ፣ ከእሱ ሰምቻለሁ ፣ ድንቅ ልጅ እና እሱ ምን አይነት ተጫዋች ነው? ባለፈው አመት ለአበርዲን ያደረገው ነገር ፍፁም ልዩ ነው በቡድን ውስጥ እና ከሙሉ ተከላካይ የምንፈልጋቸውን ነገሮች ታውቃላችሁ? እሱ ከምንፈልጋቸው ነገሮች ጋር የሚቀራረብ ልጅ ነው ስለዚህ ለረጅም ጊዜ ከእርሱ ብዙ ነገር እንጠብቃለን''

ክሎፕ ስለ ፋቢዮ ካርቫልሆ፦

''ፋቢዮ ዋው ከፉልሃም ጋር እንዴት ያለ ሲዝን ነበር ያሳለፈው በእርግጠኝነት ይህን ማየት ደስ የሚል ነበር። ማርኮ ሲልቫ እዚያ አስደናቂ ስራ ሰርቷል ነገርግን ትልቁ ክፍል ፉፁም ፋቢዮ ነበር እሱ ለእኛ የተለያዩ ቦታዎች መጫወት ይችላል የእኛ አጨዋወት መንገድ እስከ አሁን በአንድ ቦታ ላይ አልተቀመጠም ፋቢ እንደ 8 ቁጥር ፣ 10 ቁጥር ወይም ጥቂት ጡንቻዎችን ካሳደገ ሀሰተኛ 9 ቁጥር ሆኖ መጫወት ይችላል እሱ የአጭር እና የረጅም ጊዜ ፕሮጀክት ነው ነገ ሊጀምር ይችላል እና መላመድ አለበት ፣ ይህን ትንሽ ትንሽ ማየት ይችላሉ ኳስ ሲይዝ ግን ከፍተኛ ጥራት ይታያችኋል ድንቅ ተሰጥኦ ነው''

ካልቪን እና ፋቢዮን ያስፈረሙበት ምክንያት ምንድ ነው?

''በጥራት ምክንያት። ጥራት ካላህ የ 32 አመት ተጨዋች ብትሆንም ለማስፈረም ፍላጎት አለኝ ነገርግን የ18 ወይም የ19 አመት ተጨዋች ይዘህ ተመሳሳይ ጥራት ካለው በብዙ ግጥሚያዎች ላይ ለመሳተፍ እድል ይኖርሀል ይህ በጣም አልፎ አልፎ ነው ያለው እና እነሱ ይህ ነገር አላቸው''

@ethiopialivepool
1.2K viewsBoby Thiago, 04:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 07:40:45
የሊቨርፑል ሙሉ ስብሰብ ወደ ባንኮክ በመጎዝ ላይ ይገኛል

@ethiopialivepool
1.1K viewsBoby Thiago, 04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 07:40:11
1.0K viewsBoby Thiago, 04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 07:40:11
በተጨማሪም ቲያጎ እና ቫንዳይክ ቡድኑን ተቀላቅለዋል።

@ethiopialivepool
1.0K viewsBoby Thiago, 04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ