Get Mystery Box with random crypto!

New: ፊርሚኖ ቅዳሜ እለት በሊቨርፑል በቤት 100ኛ ጎሉን ማስቆጠሩ ይታወቃል እናም 100 ጎሎቹ | Liverpool Lfc sport ሊቨርፑል ኢትዮጵያ

New: ፊርሚኖ ቅዳሜ እለት በሊቨርፑል በቤት 100ኛ ጎሉን ማስቆጠሩ ይታወቃል እናም 100 ጎሎቹ 2 ጎል ብቻ በኢሊጎሬ ሲያስቆጥር 98 ጎሎቹ በጨዋታ የተቆጠሩ ናቸው።

አጥቂው አክሎም ለጎደኞቹ 70 ለጎል የሚሆን ኳስ ማቀበል ችሏል። 21 ለሳላህ ሲያቀብል 17 ለማኔ አቀብሏል እናም ቀሪውን ለሌላ ተጫዋቾች ነው ያቀበለው። በሊቨርፑል ቤት 331 ጨዋታዎችን አረጎ 170 ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ አርጓል።

በሊቨርፑል ታሪክ 19 ተጫዋቾች ብቻ ናቸው 100 ጎል ማስቆጠር የቻሉት ቦቢ ይሄንን መስራት ችሏል።

ፊርሚኖ ካስቆጠራቸው ጎሎች መካከል 57ቱ በቀኝ እግሩ ሲሆን 21 በግራ እግሩ እናም 22ቱ በጭንግላቱ ነው ማስቆጠር የቻለው በሌላ በኩል[ 93 ጎሎቹ ፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ውስጥ ነው ያስቆጠራቸው 7ቱ ደሞ ከቦክስ ውጪ ናቸው]

ከ100 ጎሎቹ መካከል አብዛኞው ያስቆጠረው ጎል ፕሪምየር ሊግ ላይ ነው [73 ጎል] እናም ይሄ በሊቨርፑል ታሪክ ስድስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል ።

21 ጎሎቹ በቻምፒየንስ ሊግ የተቆጠሩ ናቸው እናም በሊቨርፑል ታሪክ 4ተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡

• ሳላህ 34 ጎል
• ጄራርድ 30 ጎል
• ማኔ 24 ጎል
• ፊርሚኖ 21 ጎል