2021-11-06 15:45:33
#በስነልቦና_መብሰል
#Psychological_maturity
በሰው ልጅ የማደግ እና የመለወጥ ሂደት ውስጥ የሚለኩ አካላዊ እድገት እና ለውጦች ከሁለት አስርት አመታት በኋላ የሚቆሙ ቢሆንም የሰው ልጅ በስነልቦናዊ ብስለቱ ማለትም በአእምሮአዊው ፣ በስብእናው እና ማህበራዊው እድገቱ ጥራት ደረጃ ማደግ እና መለወጡን ይቀጥላል።
ይህ በሥነልቦና በቀጣይነት የመብሰል(maturity) ሂደት ለአካባቢያችን በምንሰጠው ምላሽ የነገሮችን ሁኔታ ከግዜ፣ ከቦታው እና ከአጋጣሚው ብሎም ከምንኖርበት ማህበረሰብ ባህል አንፃር በማወቅ ትክክለኛውን ባህሪ የማሳየት ችሎታ ሲሆን ለዚህ የመጎልበት ሂደት መለያው እንደ የባህሉ እና ከምናይበት ዘርፍ እንፃር ቢለያይም ከሞላ ጎደል ከአዋቂወች ቁጥጥር በመውጣት እራስን ከመቻል እና በራስ ውሳኔ የመስጠት መጀመር ጋር ይያዛል በሥነልቦና የጎልማሶች መጎልበት እና ብስለት(development and maturity ) ንድፈ ሀሳቦች እዚህ ሀሳብ ላይ ለህይወት ያለንን ትርጉም የሚጨምሩበት ሲሆን እነዚህ እሳቤዎች በአብዛኛው ከጥራት ጋር የተያያዙ እና በቀጥታ ለመለካት ከባድ እንደመሆናቸው ከሥነልቦናዊ ብስለት አንፃር እራሳችንን ለመገምገም የሚረዱ የተወሰኑ ሀሳቦች በመግለፅ ላብቃ፦
• በሥነልቦናችን እየበሰልን ስንሄድ ማውራትን በመቀነስ ማዳመጥን በመጨመር ለሌች እንዲታዩ እድል እንሰጣለን
• ሁሉንም ነገር አለማወቃችን አያሳስበንም ወይም ስህተት እንዳደለ እንረዳለን
• መተውን(ይቅር ብሎ ማለፍን) በማቆም እውነተኛ ችግሮችን ለመፍታት እንሰራለን
• ግዜ ውድ መሆኑን በመረዳት ግዜ ያችንን የሚያባክኑብንን ሰወች ወይም ነገሮች እናስቆማለን
• እራሳችንን ለሌች ብለን መጉዳትን በማቆም ለራሳችን ክብር እንሰጣለን
• ስንፈልጋቸው የምናገኛቸው እውነተኛ ጓደኞችን እንለያለን
• ሲያስፈልግ ቆፍጠን ማለት አስፈላጊ መሆኑን እንረዳለን
• ማንሾካሾክ እና የመሳሰሉት ነገሮች አላስፈላጊ፣ አሰልቺ እና ግዜን እደሚያባክኑ እንረዳለን
• በሥነልቦናችን እየበሰልን ስንሄድ አብዝተን ይቅር እንላለን፣ ለውሳኔ አንቸኩልም ብሎም ፍቅር በፍላጎት እንጂ በግፊት የሚሆን እለመሆኑን እንረዳለን።
መልካም ጊዜ!
ምንጭ
https://www.youtube.com/channel/UCy_gTy-OjVaa21gWshsuTWQ
telegram link
https://t.me/joinchat/AAAAAEaseJbULUknTizvOg
╚═════ Share ════╝
App Download የሚለዉን ይጫኑት ለማዉረድ
@abelotesfaye
361 viewsedited 12:45